Tender Detail

Tender Details

  • Deadline09 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-09 00:00:00
  • Categories Printing And Publishing

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ በ2017 ዓ.ም በዩኒሴፍ መሰረታዊ ትምህርት ፕሮግራም ለትምህርት ቤቶች አገልግሎት የሚሆን የቅድመ አንደኛ መጽሐፍት በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል፡፡


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ በ2017 ዓ.ም በዩኒሴፍ መሰረታዊ ትምህርት ፕሮግራም ለትምህርት ቤቶች አገልግሎት የሚሆን የቅድመ አንደኛ መጽሐፍት በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ በግብር ከፋይነት ተመዝግበው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፡ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና የዘመኑን የግብር ግዴታ የተወጡበትን መረጃ አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች ትምህርት ቢሮ ቁጥር 05 በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ብር 100 (አንድ መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ፋይናንሻል እና ቴክኒካል አንድ ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻው አሽገው ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 (ሀያ ሺህ ብር ብቻ) በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.አ. ወይም ባንከ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ታሽጎ በ8:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  6. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0487710688 መደወል ይችላሉ፡፡

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ

ወራቤ

 

Save Tender