Tender Detail

Tender Details

  • Company Yirgalem Medical college (የይ/ዓለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ)
  • Address ይርጋዓለም ከተማ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0909495415
  • Website
  • Deadline14 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-14 00:00:00
  • Categories Gardening And Landscaping , Building Construction

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የይርጋ ዓለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት በተቋሙ ቅጥር ግብ ውስጥ ሊያሰራ ላቀደው የግቢ ውበት እና የመግብያ በር ሥራ ለማሰራት ህጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

Yirgalem Medical college (የይ/ዓለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ)


 

የጨረታ ቁጥር 4/2017 ዓ.ም

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 4/2017

 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የይርጋ ዓለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት በተቋሙ ቅጥር ግብ ውስጥ ሊያሰራ ላቀደው የግቢ ውበት እና የመግብያ በር ሥራ ለማሰራት ህጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት፤

  1. ደረጃቸው GC 5/BC-5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የሥራ ተጫራች ለ2017 ዓ/ም ፍቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin No) ማሰረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ ከኢትዮዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለሰልጣን ወይም ከሲዳማ ክልል ኮንስትራክሽን ባለሰልጣን የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርትፊኬት ማቅረብ የምችሉ እና የተጨማሪ እሰት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፣
  2. አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎች፣ የሥራ መሳሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶችን በግላቸው አቅርበው ግንባታውን መሥራትና ማጠናቀቅ አለባቸው፣
  3. በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሰት ውስጥ ሶስት /3/ እና ከዝያ በላይ ፕሮጀክቶችን ውል ገብተው ግንባታ እያከናዎኑ ያሉ እና ያላስረከቡ ሥራ ተቋራጮች ይህን የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፡፡
  4. በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ ፕሮጀክቶችን ሰርተው ለማስረከብ ከአሰር እና ከምመለከታቸው መ/ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገብተው በስራ ወቅት ከአሰር መ/ቤት ወይም ከአማካር መ/ቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ አፈፃፀም ማስጠንቀቅያ የጠሰጣቸው የሥራ ተቃራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፣
  5. የሥራ ተቋራጮች ለውድድር የቀረቡትን ብቃት (ቴክንክ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና ኦርጅናል/ ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው፣ ይህ ተጣሪቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጭ ይሆናል፤
  6. የጨረታ ማስከበሪያ (bid security) ብር 250.000.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ) በባንክ የተረጋገጠ ዋሰትና /Bank Garanty/ ወይንም የክፍያ ማዘዣ /CPO/ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፣
  7. የሥራ ተቋራጮች በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ህጋዊ ፍቃዳቸውንና ተ.ዕ.ታ /VAT/ የተመዘገቡበት ሰርትፍኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ21/ ሃያ አንድ/ ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 5000.00/ አምስት መቶ/ ብር ብቻ በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ይርጋ ዓለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 ቀርበው በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  8. የሥራ ተቋራጮች ከጨረታው መዝግያ ቀን በፊት የግንባታ ቦታ በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው፣
  9. የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ /BID Security/ ፋይናንሻል አንድ ዋና /ኦርጅናልና /እና ሁለት ኮፒዎችን እንድሁም ቴክኒካል አንድ ዋና⁄ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒዎችን ሰነድ በተያዬ ኤንቬሎፕ በሰም ለየብቻቸው ታሽገው በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ሥምና አድራሻ በመፃፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ይ/ዓለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ ግዥ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያ ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፣
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ላይ ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም፤
  11. አሰርው መ/ ቤት የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በክፍል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
  12. አሸናፊው ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሠረት ለቅድመ ክፍያ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል፣
  13. የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በምጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል።

 

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09 09 495 415/09 11 708 366 መደወል ይቻላል፡፡

 

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የይ/ዓለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ ይ/ዓለም

 

Save Tender