በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የቡናና ቅመም ባለሥልጣን ለ2017 በጀት ዓመት ፖሊ ባግ ለመግዛት አግባብነት ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የቡናና ቅመማ ቅመም ባለሥልጣን
የፖሊ ባግ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 25/2017
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የቡናና ቅመም ባለሥልጣን ለ2017 በጀት ዓመት ፖሊ ባግ ለመግዛት አግባብነት ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ሎት ቁጥር |
የዕቃው ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ (ሲፒኦ) |
|
01 |
ለምርጥ የቡና ችግኝ ብዜት /ማፍያ/ የሚውል ፓሊቲን ቲዮብ ጥቁጥር መልክ ያለው Black color Poiythin tube ዲያሜትር (Diamater) 16 cm፤ ውፍረት (Thickness) 10 Mili-micron or 0.01cm/original መለኪያ በኪ.ግ (kg) በትክክል ጥሬ እቃ የተሰራ |
10,000 |
በመሆኑም በንግድ ዘርፍ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የVat ማስረጃ የሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለመጫረት የሚያቀርቡት ከላይ በተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ያዙበትን ሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለመጫረት ሲመጡ የመጫረቻ ሰነድ ኦርጅናል ፋይናንሻል፣ ኦርጅናል ቴክኒካል እና ኮፒ ፋይናንሻል፤ ኮፒ ቴክኒካል ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በቢሮው የተዘጋጀውን የተጫራቾች መመሪያ የጨረታ ማስታወቂያ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 50 በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 7 ቀን አየር ላይ የሚውል ሆኖ በ8ተኛ ቀን አስ/ዳይሬክቶሬት ግብርና ቢሮ ዱራሜ ቡና ቅመማ ቅመም ባለሥልጣን የግዥ ፋይ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት 1 ፎቅ ከሚገኘው በተዘጋጀው ሣጥን ተጫራቾች በዚያኑ ካስገቡ በኋላ ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ተጫራቾች (ተወካዮቻቸው በተገኙበት) ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- በእነዚህ በተጠቀሱት ቀኖች የስራ ቀን ካልሆነ ተጫራቾች ሰነዳቸውን የሚያስገቡ በሚቀጥለው በስራ ቀን ሲሆን በዕለቱ ሣጥኑን የማሸግም ሆነ የመክፈቱ ሥነሥርዓት በቅደም ተከተላቸው መሠረት በስራ ቀን የሚከናወን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የፖሊ ባጉን ናሙና ከሰነዱ ጋር አንድ ላይ ሣጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ የቢሮ ስልክ:- 046 554 2241
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የቡናና ቅመማ ቅመም ባለሥልጣን
