የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቴከኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለ2017 ዓ.ም የመኪና መለዋወጫ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቴከኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለ2017 ዓ.ም የመኪና መለዋወጫ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ከፌዴራል ሀገር ውስጥ ገቢ ወይንም ከሌሎች ግብር ሰብሳቢ የመንግሥት መ/ቤቶች ወቅታዊ የግብር ግዴታዎችን የተወጡና በመንግሥት ጨረታዎች መካፈል የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ በፌዴራል ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የመረጃ መረብ (Website) ላይ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ እና የሚጫረቱበት ዋጋ ከብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) የሚበልጥ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ 10,000 (አስር ሺ) ብር CPO ወይም የባንክ ጋራንቲ የጨረታው ሣጥን ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቴከኖሎጂ ኢንስቲትዩት አካውንት ቁጥር 1000013602728 በማስገባት ያስገቡበትን የባንክ ስሊፕ የገቢ ማመንጫ ከፍል በመቅረብ ወደ ደረሰኝ በማስቀየር የተዘጋጀውን ሰነድ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቴከኖሎጂ ኢንስቲትዩት ግዥ ሥራ አመራር ቡድን አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 101 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ብቻ በመሙላት፣ጨረታውን ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከቆየ በኋላ በዚያኑ በ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 የጨረታው ሳጥን ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይታሸጋል፡፡
- የጨረታው ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጐ በእለቱ 8፡10 በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በግዥ ሥራ አመራር ቡድን ቢሮ ቁጥር 101 ይከፈታል፡፡ (15ኛው ቀን ዝግ ከሆነ ወይም የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።)
- ኢንስቲትዩቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ግዥ ሥራ አመራር ቡድን
