በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በሀዲያ ዞን ምሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በምሻ ወረዳ በሞርሲጦ ከተማ የአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት አካል የሆነው በከተማዋ ከአዳም ቢራ መንደር ጀምሮ 0.255 ኪ.ሜትር ኮብልስቶን ንጣፍ ስራ በተዘጋጀው በዲዛይኑ መሰረት ለማሰራት በዘርፉ የተደራጁ ማህበራትን ወይም የግል ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሩ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በሀዲያ ዞን ምሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በሀዲያ ዞን ምሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በምሻ ወረዳ በሞርሲጦ ከተማ የአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት አካል የሆነው በከተማዋ ከአዳም ቢራ መንደር ጀምሮ 0.255 ኪ.ሜትር ኮብልስቶን ንጣፍ ስራ በተዘጋጀው በዲዛይኑ መሰረት ለማሰራት በዘርፉ የተደራጁ ማህበራትን ወይም የግል ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሩ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት ተወዳዳሪ ተጫራቾች፡-
1ኛ. በመስኩ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው
2ኛ. የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት ያላቸው
3ኛ. የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ያላቸው
4ኛ. የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው
5ኛ. የመልካም ስራ አፈጻጸም ሰርተፍኬት ያላቸው
6ኛ. የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ያላቸው
7ኛ. የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ያላቸው ድርጅቶች በሀዲያ ዞን የምሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ከግዥ ፋ/ን/አስ/ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 16 በአካል በመምጣት የተዘጋጀውን የግንባታ ጨረታ ሰነድ ጋዜጣው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) የማይመለስ ብር በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
8ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ሰነድ በቴክኒካል ጨረታዎች ጋር አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
9ኛ. ማንኛውም ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ መጨረሻ ላይ ዋጋውን በግልጽ በአሃዝና በፊደል መጻፍ አለባቸው፡፡ ያልተጻፈ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
10ኛ. የጨረታውን መወዳደሪያ ዋጋ ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ መሙላት አለባቸው፡፡
11ኛ. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው /አስራ ስድተኛው/ ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በ5፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
12ኛ. ተወዳዳሪ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ፖስታዎችን ቴክኒካል አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ ሰነዶች እና የጨረታ ማስከበሪያ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተወሰነ የጨረታ ማስከበሪያ እያንዳንዱን በማሸግ አራቱንም በአንድ ፖስታ በማድረግ ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ ሰነድ ሦስቱንም በአንድ ፖስታ በማድረግ እና ቴክኒካልና ፋይናንሻል በእናት ፖስታ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
13ኛ ጨረታው የቴክኒክ መስፈርቱን ካሟሉት አቅራቢዎች መካከል ዝቅተኛ ዋጋ ላቀረበው ተጫራች አሸናፊ ይደረጋል፡፡
14ኛ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0916168133/0910454656/0916673483 ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በሀዲያ ዞን ምሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
