በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጌዴኦ ዞን በዲላ ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት ለመስራት ካቀዳቸው ፕሮጀክቶች መካከል ከዚህ በታች ባለው ሳይት ግንባታ ለመስራት ባቀደው መሰረት ለመገንባት ብቁ የሆኑትንና ፍላጎት ያላቸውን ስራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጌዴኦ ዞን የዲላ ከተማ አስተዳደር
የግንባታ ብሔራዊ ግልጽ
ጨረታ (NCB) ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጌዴኦ ዞን በዲላ ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት ለመስራት ካቀዳቸው ፕሮጀክቶች መካከል ከዚህ በታች ባለው ሳይት ግንባታ ለመስራት ባቀደው መሰረት ለመገንባት ብቁ የሆኑትንና ፍላጎት ያላቸውን ስራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የግንባታ ዓይነት |
የግዥ መለያ ቁጥር |
የጨረታ ማስከበሪያ (ብር) |
ደረጃ |
|
1 |
የመንገድ ዳር አረንጓዴ ልማትና እግረኛ መንገድ ግንባታ |
DILLA/UIIDP/ CW-029/2024/25 |
120,000.00 |
GC-5 እና ከዛ በላይ |
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው:-
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ዘርፍ 2017 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ በኦን ላይን የተመዘገቡ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin no/፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፤
- የግብር ግዴታን በመወጣት ስልጣን ካለው አካል ወይም ገቢዎች ባለስልጣን ለበጀት ዓመቱ 2017 ዓ.ም በጨረታ መሳተፍ የሚያስችላቸውን የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ሠርተፊኬት የያዙ፤
- በፌዴራል ወይም በክልሉ የግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ስልጣን ከተሰጠው የሚመለከተው አካል በዘርፉ በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ /Registered in FPPA or PPA Suppliers List/
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሠነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 21 /ሃያ አንድ/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከዲላ ፋይናንስ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል የጨረታ ሠነዱን በመውሰድ በጨረታው በመሳተፍ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የተገዛውን የጨረታ ሠነድ በመሙላት እና በማዘጋጀት አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን አቀራረቡም ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በተለያየ ፖስታ ተሞልቶ እና ተዘጋጅቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካሉ ላይ ኦሪጂናል እና ቴክኒካል ኮፒ በማለት በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ እንዲሁም ፋይናንሻሉ ላይ ፋይናንሻል ኦሪጅናል እና ፋይናንሻል ኮፒ በማለት በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ እና በማሸግ ለዚህ ጨረታ ሥራ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በሃያ ሁለተኛ (22ኛው ቀን) የስራ ቀን ከሆነ ብቻ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከ2፡30 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ መግባት ይኖርበታል፡፡ ጨረታው በዚህ ዕለት በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው አከፋፈት ስነ-ስርዓትም በሁለት መንገድ ሆኖ ቴክኒካሉ በመጀመሪያ ደረጃ ተከፍቶ ከተገመገመ በኃላ ፋይናንሻል ዶክመንት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በግንባታው ስፍራ በመገኘት መስክ ምልከታ በማድረግና ከአሰሪው መ/ቤት የሳይት ምልከታ ማረጋገጫ በመውሰድ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የዲላ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጌዴኦ ዞን የዲላ ከተማ አስተዳደር
