በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ስራ ስልጠና ጽ/ቤት የአጥር ግንባታ ማሰራት ይፈልጋል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ስራ ስልጠና ጽ/ቤት የአጥር ግንባታ ማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና (ከጀርባው ይመልከቱ የሚል ኮፒ ተደርጎ መቅረብ አለበት) የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው።
- የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) የተመዘገቡ መሆናቸውን የማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የታደሠ የደረጃ 9 የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ/ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና ይጠቅመኛል የሚሉትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገነቡትን የግንባታ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
- ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 ማግኘት ይቻላል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የዕቃውን የግንባታውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ለሶስት ወር የተሰራ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ መሂ 1 ማስያዝ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለእቃና አገልግሎት ተወዳዳሪዎች ለተከታታይ 21 ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣ በ22ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል ። የውሃ ግንባታዎች ለተከታታይ 21 ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣ በ22ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል ።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ማሻሻያ ወይም ማብራሪያ ካላቸው ለእቃና አገልግሎት ግዥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታ 10 ቀናት ለግንባታ ተወዳዳሪዎች ለተከታታይ 15 ቀናት ለግ/ን/አስ/ቡድን ማቅረብ ይችላሉ።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0116250146 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
- የጨረታ መዝጊያው ቀን እሁድና ቅዳሜ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4:30 ይከፈታል።
- ተጨማሪ ስለሁሉም ጨረታዎች ማብራሪያና ማሻሻያዎች ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
አድራሻ፡- አማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከደ/ብርሃን 72 ኪሎ ሜትር ወደ ደሴ መስመር ከሚወስደው መንገድ ጣርማበር (ዋሻ) ወደ ምዕራብ 22 ኪሎ ሜትር ገባ ብሎ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
