የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በቢሾፍቱ አካባቢ ለሚያስገነባው አዲስ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት የዝግጅት ስራዎችን (Early Work Package) በቅድመ ግምገማ ብቁ የሆኑ እጩ ኮንትራክተሮችን አወዳድሮ ለመምረጥ ይፈልጋል፡፡
የእጩ ተቋራጮች ቅድመ ግምገማ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: -SSNT-T540
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በቢሾፍቱ አካባቢ ለሚያስገነባው አዲስ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት የዝግጅት ስራዎችን (Early Work Package) በቅድመ ግምገማ ብቁ የሆኑ እጩ ኮንትራክተሮችን አወዳድሮ ለመምረጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን ስራዎች ለመስራት አስፈላጊውን General or Road Contractors ደረጃ 1 የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ከሚሰጥ ህጋዊ አካል ለ2025 G.C / 2017 ዓ.ም የታደሰ ፈቃድ ያላቸው ተቋራጮች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- የሲቪል ምህንድስና ስራዎች (Earth Work and civil engineering works)
- ቁፋሮ እና ደረጃ አሰጣጥ
- ከፍተኛ ሙሌት ስራዎች (High fill works)
- ከባድ የማሽን ሥራ (Heavy Machinery Operation)
- የመሬት አቀማመጥ ጥናቶች (Topographical Surveys).
- በአውሮፕላን ማረፊያው ውስጥ እና ወደ ጣቢያው የመድረሻ መንገድ (Access Road within the airport and to site)
- የአውሮፕላን ማረፊያ ዙሪያ አጥር (Fence around the airport).
- የካምፕ ቦታ Site camp.
በተጨማሪም ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች ማሟላት አለባቸው።
- በዘርፉ ለመስራት ለ2017 ዓ.ም /2025 እ.አ.አ. ከንግድ ሚኒስቴር የተሰጠ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የሀገር ውስጥ ተጫራቾች የተሰማሩበትን የስራ ዘርፍ የሚያሳይ ህጋዊ የስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ እና በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የአቅራቢዎችና አገልግሎት ሰጪዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ መሆን ይገባቸዋል፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፣
- የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ከታክስ እዳ ነጻ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል ፣ እንዲሁም የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ውስጥ ለመሳተፍ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተሰጠ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ አንድ መቶ ብር (100.00 ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T540 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግዢ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ቴክኒካል ሠነዳቸውን ዋናውን እና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የግዥና የአቅቦት አስተዳደር ክፍል እስከ ሰኔ 02 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:30 ሰዓት ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ -
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
የግዢ እና አቅርቦቶች አስተዳደር
ስልክ ቁጥር 011-517- 8117
ብዙነሽ ዘለቀ
ኢ-ሜይል: bizuneshz@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
