የደ/ማ/ከ/አስ/ገን/መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ለሴክተር መስሪያ ቤቶች የመንግስት ሰራተኞች የመጫን አቅሙ 60 ሰውና በላይ የሆነ የሰርቪስ መኪና ለ1/አንድ ዓመት ያህል የሚቆይ በኪራይ አገልግሎት ለማግኘት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
በአብክመ ገንዘብ ቢሮ የደ/ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ገን/መምሪያ
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ማ/ከ/አስ/ገን/መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ለሴክተር መስሪያ ቤቶች የመንግስት ሰራተኞች የመጫን አቅሙ 60 ሰውና በላይ የሆነ የሰርቪስ መኪና ለ1/አንድ ዓመት ያህል የሚቆይ በኪራይ አገልግሎት ለማግኘት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህም የሚከተለውን መስፈርት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- የዘመኑና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችልና የግዥ መጠኑ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የተሽከርካሪ ሊብሬ ማረጋገጫ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማቅረብ የሚችል፤
- የግብር ከፋይ መለያ /ቲን/ ያለውና ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቾች በጨረታው ከላይ የተጠቀሰውን ዝርዝር መስፈርት ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- አሸናፊ ድርጅቱ አገልግሎቱን ደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /C.P.O/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በደ/ማ/ከ/አስ/ገን/መምሪያ ስም በተዘጋጀ መሂ-1 ደረሰኝ በመቁረጥ 200,000 /ሁለት መቶ ሺ ብር/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የደ/ማ/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ከድሮው ንግድ ባንክ ህንጻ በመምጣት በነፃ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- መኪናው የመጫን አቅሙ 60 ሰውና በላይ፣ ጌጁ የሚሰራ ከ2014 እና በላይ የተመረቱ መሆን አለበት፡፡
- አሸናፊ ድርጅቱ መኪናውን ውል ይዞ ለገንዘብ መምሪያ ካቀረበበት ቀን ጀምሮ በውል መሰረት ለመኪናው ኪራይ የሚከፍል ሲሆን ሹፌርና ነዳጅን ጨምሮ ሌሎች ወጭዎችን አቅራቢው ድርጅት የሚሸፍን ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ሰነዱን ሞልቶ በታሸገ ፖስታ ግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው በግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የደ/ማ/ከ/አስ/ገን/መምሪያ ቅጥር ግቢ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4:00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት በ4:30 ሰዓት ይከፈታል የጨረታ መክፈቻው የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ 0587713362
በአብክመ ገንዘብ ቢሮ የደ/ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ገን/መምሪያ
