ድርጅታችን ጋቴፕሮ ኃ.የተ.የግ.ማ ለጋልቫናይዜሽን የአገልግሎት ሥራ በግብአትነት እንዲውል በቅርቡ ከውጭ ያስመጣውን ጥራቱ 99.995% የሆነ 30 ቶን ዚንክ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::
GATEPRO ENGINEERING Private Limited Company (ጋቴፕሮ ኃ.የተ.የግ.ማ)
የጨረታ ቁጥር 002/2025
በድጋሚ የወጣ የዚንክ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ጋቴፕሮ ኃ.የተ.የግ.ማ ለጋልቫናይዜሽን የአገልግሎት ሥራ በግብአትነት እንዲውል በቅርቡ ከውጭ ያስመጣውን ጥራቱ 99.995% የሆነ 30 ቶን ዚንክ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::
በመሆኑም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ተሳታፊ እንድትሆኑ ይጋብዛል።
- የጨረታ መነሻ ዋጋ በአንድ ቶን ብር 950,000.00 (ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ከቫት በፊት ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች ብር 500,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በዕለቱ ይዞ መቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ለጨረታ የቀረበውን አጠቃላይ 30 ቶን ዚንክ ሳይከፋፈል ለመግዛት የቀረቡ መሆን ይገባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ይካሄዳል።
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች ጨረታው ከተካሄደበት ዕለት ጀምሮ በ 7 የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ዋጋ ተመርኩዞ የ 30 ቶን ዚንክ አጠቃላይ ገንዘብ በማስላትና የቫት ክፍያን ጨምሮ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል።
- አሸናፊው ተጫራች ዚንኩን ከመጋዘናችን ተረክቦ በራሱ ትራንስፖርት ያጓጉዛል።
- በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ገቢ ካላደረገ ለጨረታው ያስያዘው ሲፒኦ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ የጨረታው ውጤትም ይሰረዛል።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋ ሲያቀርቡ ዋጋው የተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያም እንደሚያካተት በግልጽ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
- ዚንኩን በአካል በመቅረብ ለማየት ለሚፈልጉ በማንኛውም ጊዜ በስራ ሰዓት የሚመጡ ገዥዎችን ተቀብለን የምናስተናግድ መሆኑን እየገለጽን ፣ አድራሻ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 የቤት ቁጥር 1886 ስልክ ቁጥር +251 114 40 10 70/69 እና 0952-95-24-96
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብት አለው።
ጋቴፕሮ ኃ.የተ.የግ.ማ
