በማዕ/ኢ/ሕ/ክ/መ/ የስልጤ ዞን ፋ/ል/መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ የተማሪዎች መጽሃፍት ህትመት እና ጀነሬተር በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕ/ኢ/ሕ/ክ/መ/ የስልጤ ዞን ፋ/ል/መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ የተማሪዎች መጽሃፍት ህትመት እና ጀነሬተር በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም
- በመስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ
- በተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት የሚያቀርቡ
- በመንግስት ግዥ ለመሳተፍ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ
- የጨረታ ዋስትና ለመጽሀፍት ህትመት 100,000 /አንድ መቶ ሺህ/ ብር እንዲሁም ለጀነሬተር 10,000 /አስር ሺህ/ ብር ማስያዝ የሚችሉ ተጫራቾች ሰነዱን ከስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ወራቤ ከተማ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ወራቤ ከተማ ቢሮ ቁጥር 3 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው ከወጣ በ15ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡-
መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡-0467710556 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
