Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት
  • Address ወራቤ ከተማ : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0911711864
  • Website
  • Deadline18 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-18 00:00:00
  • Categories Water Construction Machinery And Equipment , Pumps, Motors And Compressors

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት የውሃ ፓምፕ፣ ሞተርና የእስዊች ቦርድ እና አክሰሰሪ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት የውሃ ፓምፕ፣ ሞተርና የእስዊች ቦርድ እና አክሰሰሪ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

 

የሚገዛው ዕቃ አይነት

የጨረታው ማስታወቂያ ቁጥር

ጨረታው አየር ላይ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ

የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት

የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት

የጨረታው ማስከበሪያ ብር

የውሃ ፖምፕ፤ ሞተርና የእስዊች ቦርድ ከነ አክሰሰሪው

ወከው/ ..... 2017

30 (ሰላሳ ተከታታይ) ቀን

30 (ሰላሳ ተከታታይ ቀን 8፡30 በኢትዮጵያ አቆጣጠር)

በሰላሳኛው ቀን ሰዓት 8፡00 በኢትዮጵያ አቆጣጠር

30,000

 

ስለሆነም ተጫራቾች በዘርፉ፡-

  • የዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ
  • የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት
  • የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማቅረብ
  • ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ
  • የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ
  • የዘመኑ የግብር ግዴታ የተወጡ እና የከፈሉበትን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል
  • የ30,000 (ሰላሳ ሺ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ የሚችል

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከ/ወ/ከ/ው/አገ/ጽ/ቤት/ግ/ክ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 08 መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ተጫራቾች ከዚህ በላይ የቀረቡትን መረጃዎች ይዛችሁ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 (ሰላሳ ተከታታይ ቀናት) እስከ 8:00 ድረስ ብቻ በወ/ከ/ው/አገ/ጽ/ቤት/ግ/ክ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሰጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ጨረታ ስታስገቡ ሁለት ኮፒ አንድ ኦርጅናል ለየብቻ በስም በታሸገ እንድታስገቡ እንጠይቃለን፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም መታዘብ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በተገኙበት በሰላሳኛ የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው መሰረት በግልጽ ይከፈታል፡፡

ነገር ግን ሰላሳኛው ቀን በአል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታ እና ሰዓት ይከፈታል፡፡ መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ 1, የተሞላው ዋጋ መግለጫ ካልተሰጠበት ከነ ቫት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

2, የጨረታው ሰነድ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ የሌለበት መሆን አለበት፡፡

ለበለጠ መረጃ 0911711864/ 0911710769

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት

 

Save Tender