የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት በደ/ወሎ ዞን ተሁለደሬ፣ ደሴ ዙሪያና አልብኮ ወረዳዎች ባሉ ቀበሌዎች የተለያዩ የመንግስት ደን ውስጥ ያለውን የፈ/ጽድ 1836.04 ሜ/ኩ፣ ነጭ ባህርዛፍ 20,797.23 ሜ /ኩብ፤ የፈ/ግራር 20.23ሜ/ኩብ ቁም ደንና የወደቀ የደረቀ 23.24 ሜ/ኩ በድምሩ 22,676.77 ሜ/ኩብ፣ በደ/ጎንደር ደራ ወረዳ ባሉ ቀበሌዎች የተለያዩ የመንግስት ደን ውስጥ ያለውን የፈ/ጽድ 2,312.65 ሜ/ከ-ብ፣ ቀይ ባህርዛፍ 927.99 ሚ/ኩብ በድምሩ 3,240.64 ሜ/ኩብ፤ አዊ ዞን ባንጃ ወረዳ በተርያ የመንግስት ደን ውስጥ ያለውን ነ/ባህር ዛፍ 1,389.02 ሜ/ኩብ ቁም ደን ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
Amhara Forest Enterprise (የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ)
በድጋሚ የወጣ የቁም ደን ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት በደ/ወሎ ዞን ተሁለደሬ፣ ደሴ ዙሪያና አልብኮ ወረዳዎች ባሉ ቀበሌዎች የተለያዩ የመንግስት ደን ውስጥ ያለውን የፈ/ጽድ 1836.04 ሜ/ኩ፣ ነጭ ባህርዛፍ 20,797.23 ሜ /ኩብ፤ የፈ/ግራር 20.23ሜ/ኩብ ቁም ደንና የወደቀ የደረቀ 23.24 ሜ/ኩ በድምሩ 22,676.77 ሜ/ኩብ፣ በደ/ጎንደር ደራ ወረዳ ባሉ ቀበሌዎች የተለያዩ የመንግስት ደን ውስጥ ያለውን የፈ/ጽድ 2,312.65 ሜ/ከ-ብ፣ ቀይ ባህርዛፍ 927.99 ሚ/ኩብ በድምሩ 3,240.64 ሜ/ኩብ፤ አዊ ዞን ባንጃ ወረዳ በተርያ የመንግስት ደን ውስጥ ያለውን ነ/ባህር ዛፍ 1,389.02 ሜ/ኩብ ቁም ደን ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርቴፍኬት ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የሽያጩ መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተእታ (VAT) ምዝገባ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለጨረታ የቀረቡትን ቁም ደን (ምርቶች, ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ስዓት በቦታው ተገኝተው ማየት ይችላሉ ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ባሕርዳር ቀበሌ 14 አዲሱ መናኸሪያ ጀርባ እንስሳት ማዳቀያ ግቢ ውስጥ ከኢንተርፕራይዙ ቢሮ ቁጥር 20 እና በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ደ/ብርሃን፣ ደ/ታቦር፣ ደ/ማርቆስ፣ እንጅባራና ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለመግዛት የሚፈልጉትን ምርት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋሰትና (Big Bond) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን ምርት በአሪጅናል ዋጋ መሙያ ቅጽ የሚገዙበትን ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ፣ ስምና አድራሻቸውን በመፃፍ ፈርመው በመሙያው ሰነዱ ላይ ማህተም በማስቀመጥ የታሸገውን የጨረታ ፖስታ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 ፣ ደ/ብርሃንና ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የቁም ደን የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ተበሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት (ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ) እስከ መጨረሻው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ተዘግቶ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ተጫራቾች ባይገኙም ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ 15% ተእታን አይጨምርም፡፡ ሆኖም አሸናፊው በአሸነፈበት ዋጋ ላይ 15% ተእታን ጨምሮ ይከፍላል፡፡
- ተጫራቾች ቁም ደኑን በተመለከተ በቅልቅል ደንና የወደቀና የደረቀ ተብሎ ቀረብውን ክፍልፋይ ሁሉንም ክፍልፋይ ሎት /ምድብ/ በመሙላት ማንሳት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ደንበኛው ከአሁን በፊት ምርት ገዝቶ ክፍያ ያላጠቃለለ ከሆነ ክፍያ እስከሚጨርስ ድረስ ሌላ ጨረታ ላይ መሳተፍ አይችልም።
- በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በክፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ መረጃ በስልከ ቁጥር:- ባ/ዳር 058-2-26-30-95፣ ደ/ታቦር 058-4-41-03-06፣ ደ/ብርሃን 011-6-37-50-17: እንጅባራ 058-2-27-04-85: ደ/ማርቆስ 058-8-71-90-04 ኮ/ቻ 09-14-71-66-36 መጠየቅ ይችላል፡፡
የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ
