የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሥ/ክ/ኢንተ ል/ቢሮ ዳዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት ሊያሰራ ላቀደው ህጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሥ/ክ/ኢንተ/ል/ ቢሮ ዳዬ በንሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
የጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሥ/ክ/ኢንተ ል/ቢሮ ዳዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት ሊያሰራ ላቀደው ህጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
Lot-1 የኮብልስቶን ማንጠፍ ሥራ Lot-2 የሳይት ሥራ
በዚሁ መሠረት :-
- ደረጃቸው GC-7/BC-6 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የሥራ ተጫራቾች 2017 ዓ/ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No.) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ኮንስትራክሽን ሚንስቴር ወይም ከሲዳማ ብ/ክ/መ ኮንስትራክሸን ባለሰልጣን የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉና እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎች፣ የሥራ መሣሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶችን በግላቸው አቅርበው ግንባታውን መሥራትና ማጠናቀቅ አለባቸው፡፡
- በሲዳማ ከልል ውስጥ ሶስት (3) እና ከዚያ በላይ ፕሮጀክቶችን ውል ገብተው ግንባታ እያከናወኑ ያሉ እና ያላስረከቡ ስራ ተቋራጮች ይህን የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፣
- በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ ፕሮጀክቶችን ሰርቶ ለማስረከብ ከአሠሪ እና ከሚመለከታቸው መሥርያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገብተው በስራ ወቅት ከአሰሪ መስሪያ ቤት ወይም ከአማካሪ መስሪያ ቤት ማንኛውም አይነት የስራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ስራ ተቋራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፣
- የስራ ተቋራጮች ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት (ቴክኒክ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና (ኦሪጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው፤ ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክከለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ (bid security) ብር ሎት-1 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) እና ሎት-2 25,000.00 (ሃያ አምሰት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም Bid bond ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልኩ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የሥራ ተቋራጮች በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ህጋዊ ፈቃዳቸውንና ተ.ዕ.ታ (VAT) የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ21 (ለሃያ አንድ) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሥ/ክ/ኢንተ/ል/ቢሮ ዳዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ፋይናንስ ክፍል በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- የሥራ ተቋራጮች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታ ሳይት በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው።
- የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (bid bond/security) ፣ ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦሪጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን ሰነድ በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት ሥ/ክ/ኢንተ/ል/ቢሮ ዳዬ ፖሊ ቴክኒከ ኮሌጅ ፋይናንስ ከፍል ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ላይ ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም፡፡
- አሠሪው መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አሸናፊው ተጫሪች በጨረታ ሰነድ ላይ በተጠቀሰው መሰረት ለቅድመ ክፍያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0985106774/0916370231
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሥ/ክ/ኢንተ/ል/ ቢሮ ዳዬ በንሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
