Tender Detail

Tender Details

  • Company Worabe Polytechnic College (ወራቤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ)
  • Address Worabe , Central Ethiopia Regional State, Ethiopia, Phone: 0934758512
  • Website
  • Deadline09 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-09 00:00:00
  • Categories Building Construction

በማ/ኢ/ክ/መ/ የወራቤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት ለሚያስገነባው አውቶሞቲቭ ሙያ ማሰልጠኛ ማስፋፊያ የግንባታ ስራ በመስኩ የተሰማሩ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

Worabe Polytechnic College (ወራቤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በማ/ኢ/ክ/መ/ የወራቤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት ለሚያስገነባው አውቶሞቲቭ ሙያ ማሰልጠኛ ማስፋፊያ የግንባታ ስራ በመስኩ የተሰማሩ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ደረጃቸው G.C/B.C-6 እና ከዛ በላይ የሆኑ፣

  • የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ፡፡
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት የሚያቀርብ፣
  • የታደሰ የንግድ ፈቃድና የስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
  • የኮንስትራከሽንና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የዘመኑን የምዝገባ ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ፣
  • የጨረታ ዋስትና 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ማስያዝ የሚችሉ፤
  • የመስራት አቅም እንዳላቸው የሚገልፅ የወቅቱን የባንክ እስቴትመንት እና የስራ ልምድ ብቃት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  • የኦዲት ሪፖርት እና የድርጅቱን አወቃቀርና ከዚህ በፊት የሰሯቸውን ስራዎች የሚገልፅ የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ ተቋራጮች ሰነዱን ከወራቢ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር በመቅረብ ለሰነድ የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሽያል ዶክመንቱን በሚገባ በመሙላት አንድ ኦርጂናል እና 2ኮፒ ለየብቻ፣ ቴክኒካል ዶክመንቱን አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው የስራ ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ ወራቤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ፋይናንስ ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በዚሁ ዕለት 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  • ተጫራቾች ያቀረቡት የጨረታ ዋስትና ከተጠየቀው ዋጋ አንሶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛሉ፡፡
  • የተወዳዳሪ ተቋራጮች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታ መክፈቻ ቀኑን አይለውጡም፡፡
  • ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0929435907 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

ወራቤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ፋይናንስ ክፍል

 

Save Tender