በሲዳማ ብ/ክ/መ/ የዳኤላ ወረዳ ማዘጋጃ ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለቢሮ ግልጋሎት የሚውል ቤት ለመገንባት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በህጋዊ ስራ ተቋራጭ ከደረጃ 5 (አምስትና እና ከዚያ በላይ በ GC/BC) ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዳኤላ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብ/ክ/መ/ የዳኤላ ወረዳ ማዘጋጃ ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለቢሮ ግልጋሎት የሚውል ቤት ለመገንባት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በህጋዊ ስራ ተቋራጭ ከደረጃ 5 (አምስትና እና ከዚያ በላይ በ GC/BC) ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በጨረታ እንዲሳተፉ ከገቢዎች የተጻፈ ደብዳቤና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ከዚህ በፊት በሁለቱም ማለትም በ GC/BC ስራ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ያለው እና የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ከመሞላቱ በፊት በትክክል ሳይት ቪዚት ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
- ስለ ጨረታ አፈጻጸም የተዘጋጀውን ዝርዝር መረጃ እና ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) ዳኤላ ወረዳ ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት በአካል/በህጋዊ ተወካይ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21 (ሃያ አንድ ተከታታይ ቀናት) ውስጥ ሰነድ በመግዛት የሚጫረቱበትን ዋጋ ሞልተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያስገቧቸውን ሰነዶች ኦሪጅናልና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻልና ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ (ፖስታ) ይህ ግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የአስተሻሸግ ሁኔታን በተመለከተ ፋይናንሻል በአንድ ፖስታ ቴክኒካሉን ደግሞ በሌላ ፖስታ በማሸግና በመጨረሻ ሁለቱን በአንድ ፖስታ አሽጎ ማስገባት አለባቸው፡፡
- እያንዳንዱ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 55,000 (ሃምሳ አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ስሊፕ (CPO) ብቻ በመስሪያ ቤቱ ስም አሰርቶ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ከተቀመጠ ዋጋ 55,000 ብር በታች (CPO) የሚያቀርቡ ለውድድር በቂ አይሆንም፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዳኤላ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ ቤት በግዥና ን/ሥ/ህ/ክፍል ቢሮ ቁጥር አንድ ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡ ከላይ የተገለጸውን ዝርዝር መረጃ በትክክል አሟልቶ ያልፈጸመ ተጫራች ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ ፡- 0925156662/0910498942
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዳኤላ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
