የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዞናችን ባህል ቱሪዝም መምሪያ አገልግሎት የሚያስፈልግ የቪዲኦ ካሜራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዞናችን ባህል ቱሪዝም መምሪያ አገልግሎት የሚያስፈልግ የቪዲኦ ካሜራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት ተጫራቾች፡-
1ኛ በመስኩ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣
2ኛ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣
3ኛ የቫት ተመዝጋቢነት ሠርተፊኬት፣
4ኛ የዕቃ አቅራቢነት ሰርተፊኬት ያላቸው ድርጅቶች፣
በሀዲያ ዞን ፋ/መምሪያ ቢሮ ቁጥር 17 በአካል በመቅረብ የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እንድትገዙና ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 30,000 /ሠላሳ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የጨረታ መወዳደሪያ መምሪያው ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የመወዳደሪያ ፖስታዎችን አሪጅናልና ኮፒ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 17 ላይ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እንድታስገቡና ጨረታውም በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የእረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 046-1-78-42-81/ 048-5-55-23-37 ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፤
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
