Tender Detail

Tender Details

  • Company የጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address አሶሳ ፡ ቤኒሻንጉልጉሙዝ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 057-44-83-714
  • Website
  • Deadline21 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-21 00:00:00
  • Categories Communication Devices

የኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በጉምሩከ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 61 እና 62 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ስማርትና በተን ስልኮችን በሶስተኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


 

ለሶስተኛ ዙር የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር (0016/2017)

 

የኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በጉምሩከ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 61 እና 62 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ስማርትና በተን ስልኮችን በሶስተኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ከዚህ በታች በተገለፀው የጨረታ መስፈርት መሰረት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

    1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
    2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡30 እስከ 6፡00 እና ከሰዓት በኋላ 7፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ቅዳሜ ጠዋት 2፡30-6፡00 ድረስ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል በጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት ይህ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
    3. በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃ የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ዋስትና (CPO) በጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ቅ/ጽ/ቤት ስም በባንክ በተረጋገጠ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
    4. ተጫራቾች ከ08/09/2017 እስከ 13/09/2017 ከጠዋቱ 3፡45 ድረስ አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመምጣት እቃዎቹን ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ጨረታው በ13/09/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡45 ተዘግቶ በዚያው እለት ከረፋዱ 4፡00 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
    5. የጨረታው መክፈቻ ቦታ ጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡
    6. የጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን አሸናፊ ላልሆኑት ተጫራቾች ደግሞ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
    7. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ05 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
    8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ ክፍያ ከፈፀሙ በ05 ቀናት ውስጥ እቃዎቹን ተረከበው ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡
    9. ከላይ በተራ ቁጥር 7 እና 8 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ እና እቃዎቹን ተረከበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ እቃዎቹ በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባሉ፡፡
    10. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለተጨማሪ መረጃ 057-44-83-714 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender