Tender Detail

Tender Details

  • Company አ.ብ.ክ.መ. በደቡብ ወሎ ዞን የኮምቦልቻ 03 ጤና አጠባበቅ ጣቢያ
  • Address ደቡብ ወሎ ዞን : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 033 351 07 39
  • Website
  • Deadline31 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-31 00:00:00
  • Categories Electronics Materials

በኮ/ቻ ሪጅኦፖሊታንት ከተማ ጤና መምሪያ ስር የሚገኘው የኮ/ቻ 03 ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የ2017 በጀት ዓመት የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

አ.ብ.ክ.መ. በደቡብ ወሎ ዞን የኮምቦልቻ 03 ጤና አጠባበቅ ጣቢያ


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኮ/ቻ ሪጅኦፖሊታንት ከተማ ጤና መምሪያ ስር የሚገኘው የኮ/ቻ 03 ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የ2017 በጀት ዓመት የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ።

መስፈርቶቹ

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው።
  2. የግዥ መጠኑ ከ200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ ተጫራቾች ቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
  3. በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት አለባቸው። ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በመክፈቻው ቀን ባይገኙ ተቋሙ ጨረታን ከፍቶ ከማወዳደር እያግደውም፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በCPO የጠቅላላ ዋጋውን 2% ማስያዝ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በግዥ ፋይ ን አስ/ቢሮ ቁጥር 46 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
  6. የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ ይቆያል፡፡
  7. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት ኦርጂናል እና ኮፒውን ለየብቻ የታሸገ ኢንቨሎፕ በማዘጋጀት እስከ 16ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይቻላል፡፡
  8. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጧቱ 4:00 ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጧቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮ/ቻ 03 ጤና አጠ/ጣቢያ በግዥ/ፋ/ን/አስ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 46 ጨረታው ይከፈታል፡፡
  9. ጨረታ በሎት ጥቅስ ድምር ውጤት ስለሆነ የማይሞላ እቃ (አይተም) አይኖርም ያልተሞላ እቃ (አይተም) ካለ ከውድድር ውጭ ያስደርጋል ፡፡ እንዲሁም በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው በአዲሱ የግዥ መመሪያ መሰረት ከጨረታ ውጭ ያስደርጋል፡፡
  10. ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ወይም መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅቱ ማህተም እና ፊርማ ማስቀመጥ አለባቸው።
  12. ተጫራቾች በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት የተጠየቁትን መረጃዎች አሟልተሙ ካልተገኙ በጨረታው ላይ አይሳተፉም፡፡
  13. ጨረታው ለ45 ቀን ፀንቶ ይቆያል፡፡
  14. አሸናፊው በራሱ ወጭ እቃዎችን ጤና ጣቢያው ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 351 07 39 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

አ.ብ.ክ.መ. በደቡብ ወሎ ዞን የኮምቦልቻ 03 ጤና አጠባበቅ ጣቢያ

 

Save Tender