በስራና ክህሎት ሚኒስቴር በሚዛን ግብርና ቴ/ሙ/ስ ኮሌጅ ዋናው ግቢ የውሃ ስራና ፋውንቴን ስራዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
Mizan Agricultural TVET College (የሚዛን ግብርና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ)
የጨረታ ማስታወቂያ
በስራና ክህሎት ሚኒስቴር በሚዛን ግብርና ቴ/ሙ/ስ ኮሌጅ ዋናው ግቢ የውሃ ስራና ፋውንቴን ስራዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚመለከተውን መስፈርቶች ሟሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተሰማሩበትን የሚገለልፅ የታደሰ ህጋዊ የውሃ ወይም ውሃ ነክ ዘርፍ ብቻ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ቢያንስ ከደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ ተቋራጭ ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነበር ያላቸው።
- የቫት ተመዝጋቢነት የንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በዘርፉ መልካም የስራ አፈፃጸም ያላቸው እና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በካሽ ወይም በባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በአንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ በድምሩ 3 ፖስታ ሞልተው ለየብቻው በሰም የታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ አድራሻቸውን በትክክል በመግለፅ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን በሚዛን ግብርና ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ ዋናው ግቢ ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታ መስፈርት የምታሟሉ በሚዛን ግብርና ቴ/ሙ/ት/ስ ከኮሌጁ ዋናው ግቢ ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል በጽ/ቤት በመቅረብ መውሰድ ይቻላል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያው በወጣ 15ኛው የስራ ቀን በ8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ15ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት የበዓል ቀን ወይንም ዝግ ቀን ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በስራና ክህሎት ሚኒስቴር የሚዛን ግብርና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ
