ከደ/ም/ኢ/ሕ/ክልላዊ መንግስት ካፋ ዞን ሺሺንዲ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በከተማ አስተዳደር ውስጥ ሺሸንዳ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ህንፃ ግንባታ ለማስንባት ይፈልጋል።
ከደ/ም/ኢ/ሕ/ክልላዊ መንግስት ካፋ ዞን ሺሺንዲ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 1/2017
ከደ/ም/ኢ/ሕ/ክልላዊ መንግስት ካፋ ዞን ሺሺንዲ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በከተማ አስተዳደር ውስጥ ሺሸንዳ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ህንፃ ግንባታ ለማስንባት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት ተጫራቾች / ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- የVAT ተመዝጋቢ፣ TIN ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው እና በመ/መ/ቤት አቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ደረጃ 5 BC/GC እና ከዚያ በላይ የስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችልና የስራ ፍቃዱ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እና በክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ህጋዊ ማረጋገጫ የተሰጠው መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ሆኖ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ30 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ እየከፈሉ ከሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ላይ ዘወትር በሥራ ሰዓት የድርጅታቸውን ዶክመንት ይዘው በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታውን መወዳደሪያ ኦርጅናል ቴክኒካልና ፋይናንሻል ከሁለት ሁለት ኮፒዎች ጋር ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በካፋ ዞን ሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፤
- እያንዳንዱ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉት ከስራ ፍቃዳቸው ውጭ መወዳደር እና የሌላውን ተወዳዳሪ ተንተራሶ ዋጋ መሙላት አይቻልም፤
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዋጋ 100,000/ አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ማስያዝ አለባቸው፤ ጨረታ በ31ኛ የሥራ ቀናት ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይታሸጋል፤ በዕለቱ ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች (ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም።
- የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን (CPO) ለተሸናፊው ወዲያውኑ የሚመለስ ሲሆን አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን አንስቶ እስከ 7ኛው ቀን ድረስ ውሉን የማይፈጽም ከሆነ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
- የጨረታው መዝግያና መክፈቻ የሥራ ቀናት ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፤
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0476680500 መደወል መረዳት ይቻላል::
ከደ/ም/ኢ/ሕ/ክልላዊ መንግስት ካፋ ዞን ሺሺንዲ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
