መ/ቤታችን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አርባ ምንጭ ቅ/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ከመንግሥት በተፈቀደለት በጀትና በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አርባ ምንጭ ቅ/ጽ/ቤት
ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ - ESS-001-ARO-CW-2017
መ/ቤታችን በ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ከመንግሥት በተፈቀደለት በጀትና በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የግዥው ዓይነት መግለጫ |
የጨረታ ሠነድ መግዥያ ዋጋ (የማይመለስ) |
የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና መጠን በብር |
|
1 |
የእድሳት እና የአጥር የግንባታ እንዲሁም ተያያዥ ሥራዎች |
300.00 |
20,000.00 |
በመሆኑም ተጫራቾች፡-
- የጨረታ ሰነዱን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አርባ ምንጭ ቅ/ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ አስተዳደር በመምጣት 300 ብር ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣ ደረጃ 5 G.C OR 5B.C እና ከዚያ በላይ መሆናቸውን የሚያሳይ ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ማስረጃ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት፣ ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የተሰጠ ታክስ ክሊራንስ ሰርተፊኬት ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አርባ ምንጭ ቅ/ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ፣ በቅድመ ሁኔታ ያልተገደበ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የባንክ ጋራንቲ ወይም CPO ብር 20,000 ከመጫረቻ ሠነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት የግንባታ ግዥ ለተጫራቾች በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ክፍል 6 ላይ ከተመለከተው የቴክኒክ ፍላጎት ጋር መጣጣም ይኖርበታል።
- ሠነዳቸውን አንድ ኦርጂናል አንድ ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ ግንቦት 20 ቀን 2017 ዓ.ም ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው በዚሁ ቀን 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከቀኑ 8:30 ሰዓት በአዲሱ ህንጻ 1ኛ ፎቅ በግዥና ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ይህ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ይሆናል።
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ:- 0911092323/0962331133/0913929850
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት
አርባ ምንጭ ቅ/ጽ/ቤት
