በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተዉ፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን በሀራጅና በግልጽ ጨረታ እንዲሁም የተለያዩ ንብረቶችን (የተሽከርካሪ መለዋውጫዎችን ሞባይሎች፤ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮንክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
AA Kaliti Customs Office (አ.አ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት)
በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተያዙና የተወረሱ ተሽከርካሪዎችንና ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-42/2017
በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተዉ፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን በሀራጅና በግልጽ ጨረታ እንዲሁም የተለያዩ ንብረቶችን (የተሽከርካሪ መለዋውጫዎችን ሞባይሎች፤ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮንክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃ ተዘጋጅቶ ከሀሙስ ግንቦት 07 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ የሚታወቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በመሆኑም:-
- በተሽከርካሪ ጨረታ ለመሣተፍ ማንኛውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ጨረታው ከመከፈቱ አስቀድሞ ለሀራጅ ጨረታ በአክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር ባመቻቸው የማጫረቻ ሲስተም መተግበሪያ ላይ auction et በማያያዝ እንዲሁም ለግልጽ ጨረታ ከሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም በግልጽ ተሽከርካሪ ጨረታ በአክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር ባመቻቸው የማጫረቻ ሲስተም መተግበሪያ ላይ የሚሣተፍ ተጫራች auction. et ላይ በማያያዝ በጨረታው ሊሳተፍ ይችላል፡፡
- በግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል ወይም በአክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር ባመቻቸው የማጫረቻ ሲስተም መተግበሪያ auction.et ላይ በማያያዝ በጨረታው ሊሳተፍ ይችላል፡፡
- በጨረታው ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች የዕቃዎችን የግልፅ እንዲሁም የተሸከርካሪውን የግልጽ ጨረታ ሠነድ ከሀሙስ ግንቦት 07 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም የዕቃው የግልጽና የተሽከርካሪውን ሀራጅና የግልጽ ጨረታ ሰነድ በአክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር ድረ-ገፅ auction.et ላይ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ያገኙታል፡፡
- በዕቃና በተሽከርካሪ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ወይም ተሸከርካሪዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) በቅ/ፅ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የተሽከርካሪ ሐራጅ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ለሚሳተፉባቸው ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ብር 100,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በተ.ቁ 5 በተገለጸው አድራሻ ተጫራቹ ማስያዝ አለበት።
- ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ፡፡
|
ተ.ቁ |
ቅ/ፅ/ቤቱ ስም |
የጨረታው አይነት |
የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ |
የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት |
የእቃው ግልፅ |
እስከ 12/09/2017 |
በ13/09/2017 3፡45 ሰዓት ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል። |
|
የተሽከርካሪ ግልጽ |
እስከ 13/09/2017 |
በ14/09/2017 በ3፡45 ሰዓት ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል። |
||
|
የተሽከርካሪ ሐራጅ |
እስከ 13/09/2017 |
በ14/09/2017 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል። |
- የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡ እንዲሁም በበይነ መረብ (Online) የሚጫረቱ ተጫራቾች በድረ-ገፁ መከታተል ይችላሉ፡፡
- ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል፡፡
- ከላይ በተ/ቁ 10 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት CPO እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ፡- 011-4-70-85-03 እንዲሁም የአከሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በአጭር የስልክ መስመር 9164 ወይም 09-05-11-55-11/011-6-66-88-28 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡ ማሳሰቢያ፡- የተሽከርካሪ ሀራጅ ጨረታ የሚደረገው በአክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር ድረ-ገፅ መተግበሪያ auction.et ድረ-ገጽ በኦንላይን ብቻ ሲሆን በዕቃና በተሽከርካሪ ግልጽ ጨረታ ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች ከቀረቡት ሁለት የመጫረቻ አማራጮች መካከል በተመቻቸው በአንዱ ብቻ መጫረት የሚችሉ ሲሆን በአንድ ተጫራች ስም በሁለቱም አማራጮች መጫረት ከጨረታው የሚያሰርዝ ይሆናል፡፡ የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ኘሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡-
ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት፡- ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ ያለበት አዲሱ ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ
ኦክሽን ኢትዮጵያ- ቦሌ አትላስ ከለላ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢ.ቁ.301
የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
