Tender Detail

Tender Details

  • Company Belayab Motors (በላይአብ ሞተርስ ኃ.የተ.የግል ማህበር)
  • Address ቃሊቲ ብሔራዊ ት/ቤት ጀርባ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114 343691
  • Websitehttps://www.belayabmotors.com
  • Deadline23 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-23 00:00:00
  • Categories Spare Parts

በላይአብ ሞተርስ ኃ.የተ.የግል ማህበር የተለያዩ መለዋወጫዎችን (Spare parts) በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Belayab Motors (በላይአብ ሞተርስ ኃ.የተ.የግል ማህበር)


 

የመለዋወጫ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በላይአብ ሞተርስ ኃ.የተ.የግል ማህበር የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን ማለትም:- የሲኖ ትራክ (SINO Truck)፤ የኒሳን ዮዲ(Nissan UD)፤ የፋቶን ዳምፕ ትራክ (Foton Dump Truck ፎርክሊፍት (forclift) የሎደር (loader) የኤክስካቫተር(Excavator) የሪዮት ኮንትሮል (Riot Control) የዳምፐር (Damper)፤ የዜድ ኤን ኤ ፒክ አፕ (ZNA pick up) ሪች (Rich) የ ቢሾፍቱ ፒክ አፕ (Bishoftu pick up) የፎቶን ፒክ አፕ (foton pick up) የፎርላንድ (Forland) የፋዎ ቤላ (FAW BELLA)፤ የኦቲንግ (Oting) የፎቶን ሚኒ ባስ (Foton mini Bus)፤ መዳን ባስ (Mudan Bus) (ኤፍሲአር(FSB) ጋርቤጅቲፐር (Garbage Tipper) ካኒባላይዝ (Canibalize) እና ዎኪንግ ትራክተር (Walking Tractor) መለዋወጫዎችን (Spare parts) በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ እቃዎቹ አዲስ አበባ እና አዳማ በሚገኘው የድርጅቱ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች ይገኛሉ፡፡ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

    1. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመግዛት ዋጋቸውን በመሙላት ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
    2. ጨረታው የሚቆየው ጋዜጣው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ሲሆን በ11ኛው ቀን 4፡00 ተከፍቶ 4:30 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሳሪስ ቀይመስቀል ውስጥ በሚገኘው በላይአብ ሞተርስ ይከፈታል፡፡
    3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የተለያዩ መለዋወጫ እቃዎች ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
    4. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው እቃዎች ድርጅቱ ባወጣው የመነሻ ዋጋ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
    5. ተጫራቾች ሰነድ ከገዙ በኋላ ቃሊቲ ብሔራዊ ት/ቤት ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን በመቅረብ የእቃዎቹን ናሙና በአካል ማየት ይችላሉ፡፡
    6. አሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ዋጋ ከፍሎ በ15 ቀናት ውስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡
    7. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
    8. ማንኛውም ተጫራች የሚፈልገውን የመለዋወጫ ብዛት በተናጠል መጫረት ይችላል፡፡
    9. ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡

 

ከላይ በተዘረዘሩት መስፈርት ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች ሰነዱን ሳሪስ ካዲስኮ ዋና መስሪያቤት

የበላይአብ ሞተርስ ግቢ ውስጥ መውሰድ ይችላሉ፡፡

አድራሻ

 

በላይአብ ሞተርስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

ሞባይል:-096621 51 83/84

ስልክ :-0114 343691

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

 

Save Tender