በአራዳ ክፈለ ከተማ አስተዳደር በወረዳ 08 የበአታ ጤና ጣቢያ በ2017 ዓመት በጀት የሚያስፈልጉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት የበአታ ጤና ጣቢያ
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ግልጽ ጨረታ መለያ ቁጥር 02/2017 ዓመት
በአራዳ ክፈለ ከተማ አስተዳደር በወረዳ 08 የበአታ ጤና ጣቢያ በ2017 ዓመት በጀት የሚያስፈልጉ
- ሎት 1፤ መድኃኒት እና የላብራቶሪ ኬሚካሎች
- ሎት 2፤ ጥገና እና የኤሌክትሮኒክስ ጥገና
- ሎት 3፤ የተለያዩ እቃዎች
- ሎት 4፤ ህትመት
በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ መስክ የንግድ ፈቃድና የዘመኑ ግብር ለመክፈላቸውና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- መንግሥት የግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ከብር 50,000 /ሀምሳ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናችሁን የሚያረጋግጥ ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ወደ መ/ቤታችን ግቢ ማድረስ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያገለግል የተጫረቱበትን ዋጋ 2% በድርጅቱ ስም ሲ.ፒ.አ በባንክ የተረጋገጠ ከመወዳደሪያ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በአንድ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ በጥንቃቄ ሞልተው በመፈረምና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ዋናና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት (አስር ቀን) ተከታታይ የሥራ ቀን ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ ባዘገጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልቶ እና የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም አድርጎ የሚያቀርብ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- የጨረታውን አሸናፊ ማሸነፋቸውን በጽሑፍ የምንገልጽላቸው ሲሆን ለጨረታ አፈጻጸም ማስከበሪያ ላሸነፉበት እቃ ዋጋ 10% በማስያዝና ውል በመዋዋል የተመረጡትን እቃዎች በሙሉ በውሉ መሰረት ካላቀረቡት በግዢ ሕጉ መሰረት መ/ቤቱ ተጠያቂ ያደርጋል፡፡ በጨረታው ያላሸነፉ ድርጅቶች ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው አራሳቸውም ማግለል እንደማይችሉ ማወቅ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የያዘ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህን ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ጤና ጣቢያ ቀርበው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ሳጥን ይህ ማስታውቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰአት ላይ ተዘግቶ 3፡30 ላይ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት አድራሻ አራዳ ከ/ከተማ በአታ ጤና ጣቢያ አዳራሽ በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው እቃዎች በሎቶ 4፣6፣7 ያለው በሙሉ ኦርጅናል ሳምፕል ወይም ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል እንዲሁም መሥሪያ ቤቱ ድረስ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው።
- የእቃዎችን ሳምፕል እና ካታሎግ ያላቀረቡ ተጫራቾች ከጨረታ ውድቅ መሆኑን ማወቅ አለባቸው፡፡
- መሥሪያቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- አድራሻ ከሥላሴ ቤተከርስቲያን ወደ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ወረድ ብሎ በስተምስራቅ 100 ሜትር ገባ ብሎ ከመስከረም 1ኛ ደረጃ ት/ቤት አጠገብ ነው
- ስልክ ቁጥር:- 0111-8699041,011-8684810 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት የበአታ ጤና ጣቢያ
