በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር የበናፀማይ ወረዳ ፍርድ ቤት በቀይአፈር ከተማ የፍርድ ቤቱን የዙሪያ አጥር ግንባታ ለማስገንባት በዚህ መስክ የተሰማሩ ተጫራቾችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር የበናፀማይ ወረዳ ፍርድ ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር የበናፀማይ ወረዳ ፍርድ ቤት በቀይአፈር ከተማ የፍርድ ቤቱን የዙሪያ አጥር ግንባታ ለማስገንባት በዚህ መስክ የተሰማሩ ተጫራቾችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት
- ደረጃ ስድስት ጠቅላላ ወይም ህንፃ ሥራ ተቋራጭ እና ከዚያ በላይ የሆኑ።
- በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር - በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ወይም በክልሉ ከተማና መሰረት ልማት ቢሮ በኮንስትራክሽን ባለስልጣን ተመዝግቦ ለ2017 የበጀት ዓመት ከላይ በተጠቀሰው ደረጃ መሠረት የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሠርተፍኬት ያለው
- ለ2017 ዓ.ም የበጀት ዓመት በመስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው
- ለ2017 ዓ.ም የበጀት ዓመት በመስኩ የታደሰ የንግድ ምዝገባ ሠርተፍኬት ያለው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው
- ለ2017 የበጀት ዓመት በጨረታ መሳተፍ የሚያስችለውን የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት ያለው
- በተጠቀሰው የሥራ መስክ በአቅራቢነት በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ / Suppliers List Registration certificate/
- ከላይ በተገለጸው መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም አመልካች የጨረታ ሠነዱን ይህ ጨረታ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከዋለበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 21 /ሃያ አንድ/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከበናፀማይ ወረዳ ፍርድ ቤት ፋይናንስ ግዢ እና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ክፍል የማይመለስ ብር 600 /ስድስት መቶ/ በመክፈልና በመውሰድ የጨረታ ሰነዱን በሚገባ ተገንዝቦ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሠረት መወዳደር ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 / ሃምሳ ሺህ/ ብር በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሰረት በማዘጋጀት ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በማዘጋጀት አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን አቀራረቡም ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በተለያየ ፖስታ ተሞልቶ እና ተዘጋጅቶ በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካሉ ላይ ቴክኒካል ኦርጂናል እና ቴክኒካል ኮፒ በማለት በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ እንዲሁም ፋይናንሻሉ ላይ ፋይናንሻል ኦርጂናል እና ፋይናንሻል ኮፒ በማለት በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ / ለዚህ ጨረታ ሥራ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በሃያ ሁለተኛው /22ኛው ቀን (የሥራ ቀን) ከሆነ ብቻ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከ2፡30 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት ድረስ መግባት ይኖርበታል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት 6፡30 ሰዓት ታሽጎ ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር የበናፀማይ ወረዳ ፍርድ ቤት
