Tender Detail

Tender Details

  • Company በደቡብ ም/ኢ/ህ/ክ/መን/በካፋ ዞን የዋቻ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ኢኮ/ል/ጽ/ቤት
  • Address በካፋ ዞን የዋቻ ከተማ ፡ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 047-338 0625
  • Website
  • Deadline29 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-29 00:00:00
  • Categories Building Construction

የዋቻ ከተማ አስ/ር ፋይናንስና ኢ/ል/ጽ/ቤት በግልጽ ጨረታ የስቶርና የግቢ አጥር ለማሰራት ህጋዊ የግንባታ ሥራ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በደቡብ ም/ኢ/ህ/ክ/መን/በካፋ ዞን የዋቻ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ኢኮ/ል/ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የዋቻ ከተማ አስ/ር ፋይናንስና ኢ/ል/ጽ/ቤት በግልጽ ጨረታ የስቶርና የግቢ አጥር ለማስራት ህጋዊ የግንባታ ሥራ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ የግንባታ ሥራ ተቋራጮች በውድድሩ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ሀ. የመወዳደሪያ መስፈርቶች

ተጫራቾች ፡-

  1. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት እና የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤
  2. በጠቅላላ ሥራ ወይም ህንጻ ግንባታ ሥራ ተቋራጭነት ዘርፍ ደረጃ-9 (GC/BC)፤ እና ከዚያ በላይ የሆናችሁ፤
  3. ከሚመለከተው አካል የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም ለሥራ ዘመኑ አስፈላጊውን የንግድ ሥራ ፍቃድ /online

የተመዘገበና የብቃት ማረጋገጫ ዕድሳት ያደረጉ ሊሆን ይገባል፡፡

ለ. የውድድር ሂደትና የጨረታ ሰነድ አቀራረብ መመሪያ

  1. ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች በዋቻ ከተማ አስ/ር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ዋናውንና የማይመለስ አንድ ኮፒ ይዘው በአካል በመገኘት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ከፍለው የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሺያና ቴክኒካል ዶክሜንት እያንዳንዱን አንድ ኦርጅናል በተጨማሪ ሁለት ፎቶ ኮፒ ጋር ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የእያንዳንዱን ፋይናሺያልና ቴክኒካል ዶክሜንት ጥራዞች ኮፒ ለየብቻ በፖስታ እንዲሁም ኦርጅና ፋይናሺያል እና ቴክኒካል ዶክሜንት በተመሳሳይ እያንዳንዱን በየራሱ ፖስታ ካሸጉ በኋላ በአንድ ፖስታ አጠቃለው በማሸግ ቴክኒካል /ፋይናሺያል ኮፒ እና ቴክኒካል/ ፋይናሺያል ኦርጅናል በማለት) በመጨረሻም የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ ሲ.ፒ.አ (CPO) ጨረታው በእናት ፖስታ በማጠቃለል አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በሚያቀርቧቸው በእያንዳንዱ የታሸገ ፖስታ ላይ የተጫራቹ መ/ቤት ድርጅት ሙሉ ስምና አድራሻ፣ የአጫራቹ መ/ ቤት ስምና አድራሻ ጨረታው የቀረበለት ፕሮጀክት ስም እንዲሁም የዶክሜንቱ ምንነት፣ መለያ (ምሳሌ፦ ቴክኒካል ኮፒ ፣ ኦርጅናል ፋይናሻል ሲ.ፒ.ኦ (CPO).....ወዘተ በማለት) በጉልህ ጽሑፍ ማስፈር ፣ የድርጅቱን ማህተም ማሳረፍና መፈረም ይጠበቅባቸዋል።
  5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 (ሃያ አንድ) ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ22ኛው ቀን ከጧቱ ልክ 4:30 ሰዓት ላይ በዋቻ ከተማ አስ/ር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ተዘግተው በተመሳሳይ ቀንና ቦታ 8፡00 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ በጨረታው የመክፈቻ ሰዓትና ቦታ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታ መክፈቻውን ሥርዓት አያስተጓጉልም።
  6. ከላይ የተጠቀሰው 22ኛው ቀን ብሔራዊ ወይም ህዝባዊ በዓል ላይ ወይም ቅዳሜና እሁድ ላይ ሆኖ ከተገኘ የጨረታው መዝጊያም ሆነ መክፈቻ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ይካሄዳል፡፡
  7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. ይህንን ጨረታ አስመልክቶ ለማናቸውም ተጨማሪ መረጃ ከዋቻ ከተማ አስ/ር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በመድረስ አልያም በስልክ ቁጥር 047-338-0459 በመደወል አስፈላጊውን መረጃ ማግኘት ይቻላል።

 

በደ/ም/ኢት/ሕ/ክ/መ/በከፋ ዞን የዋቻ ከተማ አስ/ር ፋይናንስና ኢ/ል/ጽ/ቤት

 

Save Tender