በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ ዞን የላሊበላ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገ/ት ድርጅት አዲስ የሆኑና ያላገለገሉ የተለያዩ ኢንች መጠን ያላቸው የብረት ቧንቧ መገጣጠሚያ፤ የዲሲ አይ /DCI/ ቧንቧ መገጣጠሚያ ፤ የዩፒቪሲ /UPVC/ ቧንቧና መገጣጠሚያ ፤ የኤችዲፒ /HDP/ ቧንቧ መገጣጠሚያ እቃዎች ፤ ጀነሬተሮችና ሌሎችንም እቃዎች ጨምሮ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣው የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ መሰረት በሎት ወይም በተናጠል ሂሳብ ከፍተኛ የሽያጭ ዋጋ የተገኘውን የድርጅት ወይም የግለሰብ ሽያጭ ዋጋ በመምረጥ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በሰሜን ወሎ ዞን የላሊበላ ከተማ ውኃና ፍሳሽ አገ/ት ድርጅት
2ኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ
ሽያጭ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ ዞን የላሊበላ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገ/ት ድርጅት አዲስ የሆኑና ያላገለገሉ የተለያዩ ኢንች መጠን ያላቸው የብረት ቧንቧ መገጣጠሚያ፤ የዲሲ አይ /DCI/ ቧንቧ መገጣጠሚያ ፤ የዩፒቪሲ /UPVC/ ቧንቧና መገጣጠሚያ ፤ የኤችዲፒ /HDP/ ቧንቧ መገጣጠሚያ እቃዎች ፤ ጀነሬተሮችና ሌሎችንም እቃዎች ጨምሮ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣው የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ መሰረት በሎት ወይም በተናጠል ሂሳብ ከፍተኛ የሽያጭ ዋጋ የተገኘውን የድርጅት ወይም የግለሰብ ሽያጭ ዋጋ በመምረጥ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ፡-
- ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀትና የግብር ከፋይ መለያ ሰርተፍኬት መረጃ ወይም ነዋሪነትን ሊገልጽ የሚችል የታደሰ መታወቂያ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ በተ.ቁ 1 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻቸዉ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በላሊበላ ከተማ ውሀና ፍሳሽ አገ/ት ድርጅት ገ/ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በመምጣት ጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር ለእያንዳንዱ የሎት /ምድብ/ ሽያጭ ጨረታ ሰነድ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ ገዝተዉ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የሞሉትን የሎት /ምድብ/ ሽያጭ ዋጋ 1% በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ፖስታዉ ሳጥን ውስጥ ሲያስገቡ አብረው በፖስታው ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ይህ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ30/08/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 14/09/2017 ዓ.ም በተከታታይ ቀን በላሊበላ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገ/ት ድርጅት በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ሁሉም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን ዋና እና ቅጅ በማለት በታሸገ ፖስታ ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በዚሁ ድርጅት ቢሮ ቁ.1 በ15/09/2017 ዓ.ም ጠዋት 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ይከፈታል፡፡
- በተጠቀሰው የመክፈቻ ቀን ካላንደር ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ የመክፈቻ ቀን ለሚቀጥለው የስራ ቀን ሆኖ ከላይ በተገለጸው ሰዓት ልክ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሽያጭ ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር /10/ ቀናቶች ውስጥ ያሸነፉበትን የሽያጭ ዋጋ በሙሉ በመክፈል ዕቃዎቹን በራሳቸው ትራንስፖርት ማንሳት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ነገር ግን በተባለው ቀን ሂሳቡን ከፍሎ ዕቃዎቹን የማያነሳ የጨረታ አሸናፊ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ ውርስ ሆኖ እንደ አስፈላጊነቱ ለሁለተኛው አሸናፊ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ላይ ማብራሪያ ወይም ማሻሻያ ካላቸው ከጨረታው የጊዜ ገደብ ከ 3 ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ መሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ገ/ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 10 06 05 05 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በሰሜን ወሎ ዞን የላሊበላ ከተማ ውኃና ፍሳሽ አገ/ት ድርጅት
