Tender Detail

Tender Details

  • Company በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአዳሬ ዶሮ ዕርባታ ድርጅት
  • Address ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0980400255
  • Website
  • Deadline22 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-22 00:00:00
  • Categories Building Construction

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እንሰሳት ሀብት ልማት ቢሮ የአዳሬ ዶሮ እርባታ ኢንተርፕራይዝ ቅጥር ግቢ ውስጥ የተለያዩ የግንባታ ሥራ ለማሠራት ሕጋዊ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአዳሬ ዶሮ ዕርባታ ድርጅት


 

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እንሰሳት ሀብት ልማት ቢሮ የአዳሬ ዶሮ እርባታ ኢንተርፕራይዝ ቅጥር ግቢ ውስጥ የተለያዩ የግንባታ ሥራ ለማሠራት ሕጋዊ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት

  1. ደረጃቸው GC-7 /BC- 6 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የሥራ ተቋራጮችን በ2017 ዓ.ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱና ዘመኑን ግብር የከፈሉ ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tim No) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ወይም ከሲ/ብ/ክ/መ ኮንስትራከሽን ባለሥልጣን የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉና የተጨማሪ እሴት ታክሰ (VAT) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
  2. አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎች፤ የሥራ መሣሪያዎች፤ እና ሌሎች ሀብቶችን በግላቸው አቅርበው ግንባታውን መሥራትና ማጠናቀቅ አለባቸው።
  3. በሲዳማ ክልል ውስጥ (3) እና ከዚያ በላይ ፕሮጀክቶችን ውል ገብተው ግንባታ እያከናወኑ ያሉና ያላስረከቡ የሥራ ተቋራጮች ይህንን የጨረታ ሠነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፡፡
  4. በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ ፕሮጀክቶችን ሠርቶ ለማስረከብ ከአሠሪና ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ጉብተው በሥራ ወቅት ከአሠሪ መ/ቤት ወይም ከአማካሪ መ/ቤት ማንኛውም አይነት የሥራ አፈጻጸም ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሥራ ተቋራጮች የጨረታ ሠነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፡፡
  5. የሥራ ተቋራጮች ለመወዳደር ያቀረቡትን ብቃት (ቴክኒክ) መወዳደሪያ ሠነዶች ዋና (ኦሪጅናል) ሰነድ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተጫራቹ ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
  6. የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) ብር 40,000 (አርባ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም Bid bond ከመጫረቻ ሠነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጪ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልኩ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት አይኖረውም።
  7. የሥራ ተቋራጮች በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ሕጋዊ ፈቃዳቸውንና ተ.እ.ታ (VAT) የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ ዶክመንት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ 15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ) ብር በአዳሬ ዶሮ ዕርባታ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ክፍል በመከፈል ሠነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  8. የሥራ ተቋራጮች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታ ሳይት በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው።
  9. የጨረታው ሠነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ Bid bond security ፋይናንሻል እንድ ዋና (ኦሪጅናል) እና ሁለት ኮፒዎች እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦሪጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን ሠነድ በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸዉ ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሠዓት በአዳሬ ዶሮ ዕርባታ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ክፍል ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያው ከቴከኒካል ሠነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተገለፀው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ላይ ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም።
  11. አሠሪው መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. አሸናፊው ተጫራች በጨረታ ሠነድ ላይ በተጠቀሰው መሠረት ለቅድመ ክፍያ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  13. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0980400255/0916869180 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአዳሬ ዶሮ ዕርባታ ድርጅት

 

Save Tender