የጨረታ ቁጥር ኢመአ ሶዶ ዲስትሪክት 07/2017 ዓ/ም በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሶዶ መንገድ ጥገና ዲስትሪከት የተለያዩ ለመንገድ ግንባታ ሥራ የሚያገለግሉ የተለያዩ ዓይነት ጋቢዮን ቦክስ በግለፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሶዶ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢመአ ሶዶ ዲስትሪክት 07/2017 ዓ/ም በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሶዶ መንገድ ጥገና ዲስትሪከት የተለያዩ ለመንገድ ግንባታ ሥራ የሚያገለግሉ የተለያዩ ዓይነት ጋቢዮን ቦክስ በግለፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት በመንግሥት የግዥና ንብረት አስተዳደር መመሪያ መሠረት ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ብቁ ተጫራቾች እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የመንግስት ድርጅቶች በሚያወጡበት ጨረታ ላይ መሳተፍ እንዲችሉ በግዥ ኤጀንሲ ዌብሳይት ላይ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት በመ/ቤታችን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000322276919 የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) ገቢ በማድረግ ዘወትር በሥራ ሰዓት ወላይታ ሶደ ከነዳጅ ዲፖ አለፍ ብሎ ጎፋ ማዞሪያ አካባቢ ባለው ቢሮ በመምጣት ዝርዝር መረጃ ያያዘውን የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን 300.0000 (ሦስት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋጠ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቪሎፕ ጨረታ ቁጥሩን በመጥቀስ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት በስራ ሰዓት ከሰኞ-ዓርብ የጨረታ ሣጥኑ ከመታሸጉ በፊት በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው መሰረት በዚሁ ዕለት ከቀኑ 9፡00 ታሽጐ ከቀኑ 9፡20 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 046-551-1292 መደወል ይችላሉ፡፡
- የሚቀርበው ጋቢዮን ቦክስ ጥራቱንና ደረጃውን የጠበቀ መሆን አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ
ስልክ ቁጥር፡- 046-551-1292 ፖ.ሳ.ቁጥር 116
አድራሻ፡- ወላይታ ሶዶ ከነዳጅ ዲፖ አለፍ ብሎ ጎፋ ማዞሪያ
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሶዶ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
