የሆሣዕና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ለማኅበረሰብ ፋርማሲ፣ የመግቢያ በር እና አጥር ዮሪኖቬሽንና ጥገና ሥራን ለማሠራት የሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
የሆሣዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
የጨረታ ማስታወቂያ
የሆሣዕና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ለማኅበረሰብ ፋርማሲ፣ የመግቢያ በር እና አጥር ዮሪኖቬሽንና ጥገና ሥራን ለማሠራት የሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት
- ደረጃቸው BC-7 / GC-7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል የጨረታ ሰነዱን ከኮሌጁ ግዥ ፋይ/ን/አስተዳደር ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20ኛው ቀን ድረስ 400 /አራት መቶ ብር/ የማይመለስ በሆሣዕና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሣብ ቁጥር 1000021172867 በመክፈል ባለፈቃዱ ወይም ሕጋዊ ተወካዩ አንድ ኮፒ የሰነድ ማስረጃ በመያዝ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በኮሌጁ ስም 30,000 /ሰላሣ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /Unconditional bank guarantee letter/ ከፋይናንሻል ሰነድ ጋር በፖስታ በሰም አሽገውና ማህተም በማድረግ ፈርመው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች አስፈላጊውን ዕቃና ሠራተኞች አቅርቦ ሥራውን የሚሠሩበትን የፋይናንሻል ፕሮፖዛል አንድ ኦርጂናል ሁለት ፎቶ ግራፍ ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዶችን ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እንዲሁም አራቱን ሰነዶች በሌላ አንድ ማጠቃለያ ፖስታ በሰም አሽገውና የፕሮጀክቱን ስም ጠቅሶ የቴክኒካል ፕሮፖዛል አንድ ኦርጂናል ሁለት ፎቶ ግራፍ ከኮፒ ሰነዶች እንዲሁም ኦርጂናል ቴክኒካል ሀሳብ የያዘ ሰነድ Bidder Certification of Compliance/ ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ አራቱን የቴክኒካል ሰነዶች በሌላ ማጠቃለያ ፖስታ በሰም አሽጐ ሁለቱንም የቴክኒካል እና የፋይናንሽያል አቃፊ ፖስታዎች በአንድ ማጠቃለያ እናት ፖስታ በማድረግ የፕሮጀክቱ ስም ጠቅሶ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ተከታታይ 21ኛው ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል። በእጅ የተሞሉ ሰነዶች ማቅረብ ከጨረታው ውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡ የአገልግሎት ዋጋው በሰነድ ላይ በተዘጋጀው ቦታ በአሃዝና በፊደል መሞላት ይኖርባቸዋል፡፡ ኦርጂናል የቴክኒካል ሀሣብ የያዘ ሰነድ /Bidder Certification of Compliance/ አለመመለስ ከጨረታ ውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
- ጨረታው በ21ኛው ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ ግዥ ፋይ/ን/አስተዳደር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ 21ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ አሠሪው መ/ቤት የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፦
-
- የተሻሻለው የቀድሞ የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት የግዥ መመሪያ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ከወቅቱ ከገበያ ዋጋ በታች ያቀረበ እንደሆነ ኮሌጁ በሥራው ውል ለመግባት አይገደድም
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0913568248 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የሆሣዕና ጤና ሣይንስ ኮሌጁ
ሆሣዕና
