በአማራ ክልላዊ መንግስት በምስ/ጎጃም ዞን አስተዳደር የደጀን ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ለአዲሱ የነፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ዝርጋታ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የኤሌክትሮ መካኒካል ዕቃዎች፤ ሎት 2 የውሃ ጥራት ማረጋገጫ ኪት እና ባዮሎጂካል ቴስት ሪኤጀንት በግልጽ ጨረታ ህጋዊ ተጫራቾችን በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር የደጀን ከተማ ውሃ አገ/ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ክልላዊ መንግስት በምስ/ጎጃም ዞን አስተዳደር የደጀን ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ለአዲሱ የነፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ዝርጋታ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የኤሌክትሮ መካኒካል ዕቃዎች፤ ሎት 2 የውሃ ጥራት ማረጋገጫ ኪት እና ባዮሎጂካል ቴስት ሪኤጀንት በግልጽ ጨረታ ህጋዊ ተጫራቾችን በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይገልጻል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ እና የግብር መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፤
- የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዙ እቃዎችን እይነት እና ዝርዝር መግለጫ /Specification/ ከጨረታው ሰነድ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 50.00 / ሃምሳ ብር / በመክፈል ከደጀን ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ሎት የዕቃውን 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሀሳባቸውን በአንድ ኮፒ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ አሽገው የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም እና አድራሻቸውን በመሙላት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ ደጀን ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 ላይ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚችሉ እና የጨረታው ሳጥን በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ /ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ደጀን ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 የሚከፈት ሆኖ 16ኛው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ቦታ እና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙ ጨረታውን ከመክፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታው ሂደት ያልተገኙ ተጫራቾች በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚያዝበት ወቅት ያሸነፈበትን ዕቃ ዋጋ 10% የውል ማከበሪያ በባንክ ተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው አሽናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፈበትን ዕቃ /ንብረት/ ጠቅላላውን ወጪ በመሸፈን ደጀን ከተማ ውሃ አገ/ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ውድድሩ በነጠላ ወይም በጥቅል ዋጋ (ሎት) ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከደጀን ከተማ ውሃ አገ/ጽ/ቤት ከገቢ ግ/ፋ/ን/አስ/ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058-7-76-17-15 /058-7-76-00-15 /በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል ፡፡
በአብክመ በምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር የደጀን ከተማ ውሃ አገ/ጽ/ቤት
