በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ለቢሮው አገልግሎት የሚውል የፎቶ ካሜራ ከነ ሙሉ አክሰሰሪው በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Central Ethiopia Regional State Health Bureau (በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ)
በድጋሚ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ለቢሮው አገልግሎት የሚውል የፎቶ ካሜራ ከነ ሙሉ አክሰሰሪው በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት፡
|
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
ጨረታው አየር ላይ የሚቆይበት እና ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት |
ምርመራ |
|
1 |
የፎቶ ካሜራ ከነሙሉ አክሰሰሪው |
ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ ውሎ በዚያው ዕለት በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል። |
በቀረበው ስፔስፍኬሽን መሰረት ዝርዝር መረጃውን በጨረታ ሰነዱ ላይ ይመልከቱ |
በመሆኑም ተጫራቾች፣
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፤፤
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በላይ ሲሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በከልሉ ጤና ቢሮ ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋና ዶክመንታቸውን የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.አ ጨምሮ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ የጨረታ ማስከበሪያውን ሲፒኦ ለየብቻ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ይውላል፡፡ ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ጨረታው በቢሮው ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ለዚሁ ስራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- 15ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት እና ቦታ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የጨረታው ውጤት እንደታወቀ ውል የሚፈጽም ሲሆን ያሸነፈውን ዕቃ ንብረት ከክልል ጤና ቢሮ ወራቤ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
- ቢሮው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ 0463269 229
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ
