የከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ጨረታ ቁጥር አንድ (1) ለእንጨት ብረታ ብረት ሥራዎች ለትምህርትና ሥልጠና፣ ለመሰረተ ልማት፤ ለጥገና ለግንባታ፤ የጌጥ ዛፎች ሀረጎች እና የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽ ማስወገጃ የመኪና ኪራይ አገልግሎት የሚውል የጥሬ እቃ ግብእቶች በግልፅ ጨረታ መግዛት አስፈልጓል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል ከዚህ በታች የተጠቀሱትን፡-
ጨረታ ቁጥር አንድ (1) ለእንጨት ብረታ ብረት ሥራዎች ለትምህርትና ሥልጠና፣ ለመሰረተ ልማት፤ ለጥገና ለግንባታ፤ የጌጥ ዛፎች ሀረጎች እና የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽ ማስወገጃ የመኪና ኪራይ አገልግሎት የሚውል የጥሬ እቃ ግብእቶች በግልፅ ጨረታ መግዛት አስፈልጓል።
በዚሁ መሠረት፦
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ፣ በሥራው መስክ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በዕቃ ግዢና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበት የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ እና መለያ ቁጥር (Tin Number) ተመዝጋቢ የሆኑና የተሟላ ማስረጃ ሊያቀርቡ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን አንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት ብር) ለእያንዳንዱ ሰነድ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000007971188 ገንዘቡን ገቢ በማድረግ ከፍተኛ ጥበቃ ማረ/ቤት ማዕከል ገዥ ክንውን ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡ ማረ/ቤቱ የሚገዛቸውን ዕቃዎች ዝርዝር በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ተዘርዝሮ ቀርቧል፡፡
- ተጫራቾች ከላይ በጨረታ ቁጥር 1 ለተጠቀሱት ጨረታዎች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚመለስ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች አንዱ በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ናሙና እንዲያቀርብ የተጠየቀባቸው ናሙናውን በጨረታ መክፈቻ ቀን ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምር የጨረታ ሠነድ መግዛትና የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ቁጥር 1 ሚያዝያ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዳቸውን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለቱ በ4፡15 ሰዓት በማረ/ቤቱ በግዥ ክንውን ቡድን ቢሮ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ከፍተኛ ጥበቃ ማረ/ቤት ማዕከል ገላን በሚገኘው ዕቃ ግ/ቤት አስቸኳይ ስለሆነ በአንድ ጊዜ አምጥተው ያስረክባሉ፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
- ማረሚያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች ፕሮፎርማቸው ላይ ዋጋ ሲፅፉ ስርዝ ድልዝ የሌለበት ጎላ ብሎ የሚነበብ ጽሑፍ መሆን ይገባዋል ስርዝ ድልዝ የተሞላ ዋጋ ተቀባይነት የለውም ይጠበቅባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ቃሊቲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000007971188 አ/አ ማረ/ቤት እደ-ጥበባት ማዕከል በሚል ገንዘቡን ገቢ ካደረጉ በኋላ መግዛት ይችላሉ።
አድራሻ፦ አባ-ሳሙኤል ማረሚያ ማዕከል
ስልክ ቁጥር፡- 011-4-39-76-61-011-8-88-91-81
በፌዴ/ማረ/ቤት ኮሚሽን የከፍተኛ ማረሚያ ማዕከል
