Tender Detail

Tender Details

  • Company Sidama National Regional State Revenue Authority (የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ባለሥልጣን)
  • Address ሀዋሳ ከአሮጌ መናኸሪያ ጀርባ 300 ሜትር ገባ ብሎ ፡ ሀዋሳ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0462125156
  • Website
  • Deadline23 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-23 00:00:00
  • Categories Building Construction

ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ባለሥልጣን በ2017 ዓ.ም ለቢሮ ሠራተኞች የሚሆን ካፌ ግንባታ እና የሰብሰባ አዳራሽ ጥገና አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Sidama National Regional State Revenue Authority (የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ባለሥልጣን)


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ባለሥልጣን በ2017 ዓ.ም ለቢሮ ሠራተኞች የሚሆን ካፌግንባታ እና የሰብሰባ አዳራሽ ጥገና አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ ድርጅት በጨረታው እንዲሳተፍ እየጋበዝን በጨረታው ላይ ለመካፈል ተቋራጩ ቀጥሎ የቀረቡትን መመዘኛዎች ወይም መስፈርቶችን ማሟላት ይኖርበታል፡፡

  1. ተቋራጮች GC -6/BC 5 እና ከዛ በላይ ሆኖ በ2017 የታደሰ፣ የግብር ካፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የአቅራቢዎች የምዝገባ ምስከር ወረቀት ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው የሚገልጽ መረጃ ማቅረብ አለባቸው:
  2. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21/ ሃያ አንድ ተከታታይ ቀናት ከፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
  3. የጨረታውን ዝርዝር ሁኔታ የሚያመላክት የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21ቀናት ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ተከታታይ ቀናት ውስጥ የንግድ ፍቃዳቸውን በመያዝ ቀርበው ከቢሮ ቁጥር 24 በ 400 መቶ ብር በመግዛት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. ለጨረታ ማስከበሪያ 60,000 በባንክ የተመሰከረ CPO ብቻ በፖስታ አሽገው ማስያዝ አለባቸው፡፡
  5. ጨረታው በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 በክልሉ ገቢዎች ባለስልጣን ግዥ ፋይ/ንብ/ አስ/ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 24 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ቀኑ በዓል ወይም የአረፍት ቀናት ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች የፋይናንሻልና የቴክኒክ መገምገሚያ መስፈርት በመሙላትና በተለያየ አንድ ኦርጅናል 2ኮፒ በማሸግ በፖስታው ላይ የፋይናንስና የቴክኒክ መሆኑን በመግለጽ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የሰጡት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታከለ ማካተት አለማካተቱን በፋይናንሻል ጨረታ ዋጋ ማቅረቢያው ላይ በግልጽ ማሳየት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሆኖም ካልተገለፀ የተሰጠው ዋጋ ታክስን ያካተተ እንደሆነ ይቆጠራል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን አልወዳደርም ማለት አይችልም፡፡
  9. የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉ በፅሁፍ ከተገለጸለት በኋላ በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ለውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተመሰከረ CPO በመያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል መፈራረም አለበት፡፡ ውሉን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ባይገባ ባይፈጽም የጨረታ አሸናፊነቱ ይሰረዛል፡፡
  10.  የጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅትን ወክሎ ውሉን የሚፈርም የድርጅቱ ባለቤት ሳይሆን ቀርቶ ተወካይ ከሆነ ህጋዊ ውክልና ኦርጅናልና የማይመለስ ኮፒ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  11.  የጨረታው የውል ማስከበሪያ የተያያዘው ገንዘብ አሸናፊ ተጫራች ግዴታውን በውሉ መሠረት ካልፈጸሙ በውሉ ላይ በሚገለጸው ህግ መሠረት መ/ቤቱ ተፈጻሚ የማድረግ መብት አለው።
  12.  ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ ፡- ሀዋሳ ከአሮጌ መናኸሪያ ጀርባ 300 ሜትር ገባ ብሎ እንገኛለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0462125156 ይደውሉ፡፡

 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ባለሥልጣን

 

Save Tender