Tender Detail

Tender Details

  • Company የኦሮሚያ ቡና ገበሬዎች ሕብረት ሥራ ዩኒዬን ኃላፊነቱ የተወሰነ
  • Address ሸገር ከተማ አስተዳደር ገላን ክፍለ ከተማ አካባቢ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 251911226744
  • Website
  • Deadline23 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-23 00:00:00
  • Categories Printing And Publishing

የኦሮሚያ ቡና ገበሬዎች ሕብረት ሥራ ዩኒዬን ኃላፊነቱ የተወሰነ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የማሸጊያ ዕቃዎችን ከሀገር ውስጥ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።

የኦሮሚያ ቡና ገበሬዎች ሕብረት ሥራ ዩኒዬን ኃላፊነቱ የተወሰነ


 

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር: OCFCU/04/2017

 

የኦሮሚያ ቡና ገበሬዎች ሕብረት ሥራ ዩኒዬን ኃላፊነቱ የተወሰነ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የማሸጊያ ዕቃዎችን -

  1. Paper bag duplex full color print, laminated with supporter having logo,
  2. Cake box with logo.
  3. Double walled paper take-away cups with full color having logo and
  4. Cup holders for outdoor service with full color having logo.

ከሀገር ውስጥ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚታሟሉ ተጫራቾች፡-

  1. በዘመኑ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው፤
  2. ንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  4. የግብር ከፋይ ምዝገባ (ቲን ነምበር) ማቅረብ የሚችል፤
  5. አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበበትን መረጃ ማቅረብ የሚችል፤
  6. የዘመኑ ግብር መክፈሉ የሚያረጋገጥ የምስክር ወረቀት ክሪላንስ ማቅረብ የሚችል፤
  7. አስፈላጊ ሙያ ብቃት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል፤
  8. ተወካይ ከሆነ/ከሆነች ህጋዊ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ተጫራች፤
  9. የመጫረቻ ሰነድ የማይመለስ ብር 800.00 (ስምንት መቶ ብር) በኦሮሚያ ቡና ገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒዬን ኃላፊነቱ የተወሰነ (OCFCU) በሚል በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000369311747 ወይንም በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000005951163 ገቢ በማድረግ ያስገቡበትን ደረሰኝ በመያዝ ከዩኒዬኑ ዋና ካሸር 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሃያ አንደኛው ቀን (21) ተከታታይ የስራ ቀናት ከሰኞ እስከ ዓርብ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00፤ ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 11፡00 እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰነዱን ማገኘት ይችላሉ፡ ሆኖም በዩኒዮኑ አሰራር መሰረት ቅዳሜ የስራ ቀን በመሆኑ እንደ ስራ ቀን ይቆጠራል፤
  10.  ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 2% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የክፍያ ማዘዣ በCPO በኦሮሚያ ቡና ገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒዬን ኃላፊነቱ የተወሰነ በሚል ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ፤ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ከአዋሽ ባንክ ወይንም ከኦሮሚያ ባንክ ብቻ በማሰራት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  11.  ተጫራቹ የመጫረቻ ሰነድ ሲያቀርቡ ኦርጅናል እና ኮፒ ብሎ መለየት ይኖርባቸዋል፤
  12.  ተጫራች ለሚጫረት ዕቃ ናሙና ማቅረብ ግዴታ ነው፤
  13.  የጨረታ መክፈቻ ቀን በተመለከተ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በ22ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ በዩኒዬናችን 3ኛ ፎቅ መሰብሰቢያ አዳራሽ በሚገኘው ሳጥን ውስጥ ሰነዱን በማስገባት እና በዚሁ ቀን በ4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ፤ ሆኖም 22ኛው ቀን የስራ ቀን ላይ ካልዋለ የሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፤
  14.  የጨረታ ዋጋው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ45 የስራ ቀናት ይሆናል፡፡
  15.  ዩኒዬኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡- ሸገር ከተማ አስተዳደር ገላን ክፍለ ከተማ አካባቢ የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ ገላን ቅርንጫፍ ያለበት ሕንፃ ላይ ነው ኦሮሚያ ቡና ገበሬዎች ሕብረት ሥራ ዩኒዬን ኃላፊነቱ የተወሰነ

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0114450046

ሞባይል፡- +251911226744/+251917851854

 

የኦሮሚያ ቡና ገበሬዎች ሕብረት ሥራ ዩኒዬን ኃላፊነቱ የተወሰነ

 

Save Tender