በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የቃሊቲ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ስራዎች ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን በማሟላት የሚሰሩ ስራ ተቋራጮች በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨርታ ቁጥር 003/2017
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የቃሊቲ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ስራዎች ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን በማሟላት የሚሰሩ ስራ ተቋራጮች በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ሎት 1 - በግቤው ውስጥ ልዩ ልዩ አገልግሎት መስጫ ክፍሎችን መገንባት እና ማደስ
- ደረጃቸው GC/BC 5 እና ከዚያ በላይ
- ለስራው ንግድ ምዝገባና ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የ2017 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እና በ2017 በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉ፣ ከፌዴራል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚ/ር የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ለ2017 በጀት ዓመት የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው (ከሁለቱም) ፤ የአቅራቢነት ምዝገባ ያላቸው (Supplier List)፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው::
- ስራ ተቋራጮች የሚወዳደሩበትን ፋይናንሻል ሰነድ አንድ ኦርጂናል እና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ በድምሩ ሁለት ሰነድ የድርጅቱን ፊርማ፤ ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የፕሮጀክት ስም እና ሎት በመጻፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናም (BID BOND or BID SECURITY) በባንክ ትእዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና UNCONDITIONAL BANK GUARANTEE/ ለብቻ በታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱን ፊርማ እና ማህተም በማድረግ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ ሁለቱንም ፖስቶች በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም፤ ፊርማ እና የሚወዳደሩበትን የፕሮጀክት ስም እና ሎት በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር (10) ተከታታይ የስራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱ ሽያጭ ዘወትር በስራ ሰአት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡30 ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በቃሊቲ ጤና ጣቢያ አቢሲንያ ህንፃ 2ኛ ወለል ላይ በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 30 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናው (Original) እና የማይመለስ ቅጂ (Copy) ይዞ በመቅረብ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቶች የወሰዱትን ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀን ከቆየ በኋላ በአስራ አንደኛው (11) ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችዋል፡፡ የጨረታ ሳጥን በዚሁ ሰዓት ታሸጎ 4፡30 ሰአት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በቃሊቲ ጤና ጣቢያ አቢሲንያ ህንፃ 2ኛ ወለል በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 30 የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND) በብር 120,000.00 ብር ለ 90 ቀናት የሚያገለግል ወይም የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND or BID SECURITY) በባንክ ትእዛዝ (CPO) ወይም/ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /UNCONDITIONAL BANK GUARANTEE የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- አሰሪ መስሪያ ቤቱ ወቅታዊ የገበያ ዋጋን ላላገናዘበ ስራ ዝርዝር ማለትም ከገበያ ዋጋ የተጋነነ ነጠላ ዋጋ (Unit Rate) (በከፍታ ወይም በዝቅታ) ተሞሎቶ ካገኘ ስራ ተቋራጮች (Cost Break down) ሰርተው እንዲያቀርቡ ያስገድዳል።
- አሰሪ መስሪያ ቤቱ በዋጋ ላይ ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ (Unsigned Rate Correction) እና በዋጋ ላይ ፍሉድ መጠቀም (to use fluid for Rate Correction) ከጨረታ ተወዳዳሪነት ያሰርዛል፡፡
- በስራ ዝርዝር በሙሉም ሆነ በአንድ የስራ አይተም ላይ ዋጋ አለመሙላት (unfilled rate) ከተገኘ ስራውን በነጻ እንደሚሰራ ይወሰዳል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከማስገባታቸው በፊት የተጫራቾች መመሪያን እንዲያነቡ እና የግንባታ ሳይቱን ማየት ይመከራል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በቃሊቲ ጤና ጣቢያ አቢሲንያ ህንጸ 2ኛ ወለል ከላይ በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 30 ወይም 0118595055 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአቃ/ቃ/ክ/ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የቃሊቲ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ
