Tender Detail

Tender Details

  • Company የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት
  • Address ቢሾፍቱ ከተማ : ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-437-16-83
  • Website
  • Deadline15 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-15 00:00:00
  • Categories Merchandise

በአሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ለ2017 ለሥራ የሚገለገልበትን ሶፍት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ለ2017 ለሥራ የሚገለገልበትን ፡-

Lot.1 Soft በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትይፈልጋል፡፡

የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

  1. ህጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (VAT) ያላቸው።
  3. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በሌላም በሚመለከታቸው ፍቃድ ሰጪ አካላት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች ብቻ መካፈል ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስራ አምስት (15) ተከታታይ ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በመ/ቤቱ ቀርቦ መግዛት ይችላል።
  5. ለጨረታው ማስከበሪያ ጠቅላላ ካቀረቡት የዕቃ ዋጋ ብር 1% በተረጋገጠ ባንክ (cpo) በድርጅቱ ስም አሰርቶ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል፡፡
  6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የእቃውን ስፔሲፊኬሽን ከድርጅቱ በቀረበው መሠረት በግልፅ በመፃፍና ዕቃው ላይም በግልፅ መታየት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፁትን ማንኛውም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁማለት አይችልም፡፡
  8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫት ያጠቃለለና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎችን አሟልተው በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ የቢሾፍቱ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ቀርቦ ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ በ10 ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ተከታታይ ቀናት ጠብቆ በ15ኛ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ጨረታው ተዘግቶ በዛው ቀን 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ በእለቱ በአል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው።
  11. ድርጅቱ ከሰጠው ስፔስፊኬሽን ውጪ ማስተካከያ ማድረገ እና መሰረዝ (Material Devation) አይቻልም ።
  12. ተጫራቾች በድርጅቱ በዋጋ ማቅረቢያ የድርጅቱ ኦርጅናል ማህተም (የቢሾፍቱ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት የሚል ማህተም) ባረፈበተ ላይ ብቻ የዕቃ ዋጋዎችን ሞልቶ ማቅረብ አለበት፡፡ ከድርጅቱ ዋጋ ማቅረቢያ ውጪ የሚመጡ ሰነዶች ዋጋ የላቸውም፡፡
  13. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ድርጅታችን ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክተር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር

011-437-16-83 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡

 

የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት

 

Save Tender