ትራንስ ኢትዮጵያ ሃ/የ/የግ/ማሕበር መቐለ በሚገኘው ዋና ቢሮ ቤት በተለያዩ ቦታዎች የደህንነት ካሜራ (Security Camera) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ገዝቶ ለማስገጠም ስለ ፈለገ በዘርፉ የተሰማራቹ አቅራቢዎች ከዚህ በታች የተገለፁ ነጥቦች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ እንጠይቃለን።
Trans Ethiopia PLC (ትራንስ ኢትዮጵያ ኃላ.የተ.የግል ማህበር)
ትራንስ ኢትዮጵያ ኃላ.የተ.የግል ማህበር
Trans Ethiopia PLC
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ሰነድ ቁጥር 006/2024/2025
ትራንስ ኢትዮጵያ ሃ/የ/የግ/ማሕበር መቐለ በሚገኘው ዋና ቢሮ ቤት በተለያዩ ቦታዎች የደህንነት ካሜራ (Security Camera) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ገዝቶ ለማስገጠም ስለ ፈለገ በዘርፉ የተሰማራቹ አቅራቢዎች ከዚህ በታች የተገለፁ ነጥቦች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ እንጠይቃለን።
- ተጫራቾች በተጠቀሰው ዘርፍ የ2017 ዓ/ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ አለባቸው። የ 2017 ዓ/ም ንግድ ፍቃድ ያላሳደሰ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል። የ2017 ዓ/ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ በዋናው (Original) ቴክኒካል ጨረታ ሰነድ ውስጥ ታሽጎ መቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑን በግልፅ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡ ይህ ካልተገለፀ የቀረበው ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ (Vat) እንዳካተተ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ድርጅታች በሰጣቸው ፋይናንሻል ጨረታ ሰነድ ብቻ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ ስርዝ ድልዝ ያለበት መሆን የለበትም። ስርዝ ድልዝ ያለበት ሰነድ ያቀረበ ተጫራች ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበርያ (Bid Bond) ባቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% በትራንስ ኢ/ያ ኃ/የተ/የግ/ማሕበር ስም የተዘጋጀ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው ። ጠቅላላ ዋጋ ማለት ያቀረቡት የሁሉም ዕቃዎች ድምር ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ (Vat) ጨምሮ ማለት ነው፡፡ የሚቀርብ ሲፒኦ ለብቻው ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡ ሲፒኦ ያላቀረበ ወይም በተጠቀሰው መጠን መሰረት ያላስያዘ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል።
- አሸናፊ የሆነ ተጫራች ላሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ (ተጨማሪ እሴት ታክስ ጨምሮ) ውል ማስከበርያ (Performance Bond) 10% ማስያዝ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ፋይናንሻልና ቴክኒካል ጨረታ ሰነድ በመቐለ ዋና ቢሮ በዳይሬክተር ግዢና የአቅራቢዎች ትስስር ቢሮ እንዲሁም በአዲስ አበባ ሳሪስ አካባቢ በሚገኘው ትራንስ ታወር ላይዘን ኦፊስ የማይመለስ ብር 500 በመክፈል መውሰድ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እስከ ውል ሚታሰርበት ቀን ለ 90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይመሆኑ ማወቅ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀን ውስጥ ውል ማስር አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ ከመሙላታቸው በፊት እንዲሁም ጨረታው ከሚከፈትበት 5 ቀን በፊት ወደ መቐለ ቢሮ በአካል በመምጣት እያንዳንዱ የደህንነት ካሜራ የሚገጠምበት ቦታ የማየት ግዴታ አለባቸው፡፡
- አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች መቐለ በሚገኘው ዋና ቢሮ ያሸነፉት ዕቃ በራሳቸው መጓጓዟ ማቅረብና መግጠም አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በታሸገ ፖስታ እስከ ግንቦት 12/2017 ዓ/ም ጠዋት ሰዓት 3:30 በመቐለ ዋና ቢሮ በዳይሬክተር ግዢና የአቅራቢዎች ትስስር ቢሮ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ፋይናንሻልና ቴክኒካል ፕሮፖዛል ኦርጅናልና ፎቶኮፒ ለየብቻ ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ግንቦት 12/2017 ዓ/ም ጠዋት 3:30 ሰአት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ጠዋት 4:00 ሰአት በመቐለ ዋና ቢሮ በዳይሬክተር ግዢና የአቅራቢዎች ትስስር ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- የጨረታ ሰነድ በተቀመጠው የጨረታ ማስታወቅያ መሰረት የተሟላ ከሆነ ተጫራቾች ባይገኙም ይከፈታል፡፡
- ድርጅታችን ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ ወይም ግልፅ ያልሆነላቸው ሃሳብ ተጫራቾች በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 0914007732/0911867040 በሥራ ሰዓት ደውላቹ መጠየቅ ትችላላቹ።
ትራንስ ኢ/ያ ኃላ/የተ/የግ/ማሕበር
