በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የጎፋ 2 አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት (17-05B) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አባሪ ሆነው የተዘረዘሩትን ለሳይትዎርክ ሥራ የሚውል ማለትም "Supply and Construct Stone Masonry Works" ስራዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የጎፋ 2 አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት (17-05B)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/17-05B/gofa 00107/2017
በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የጎፋ 2 አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት (17-05B) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አባሪ ሆነው የተዘረዘሩትን ለሳይትዎርክ ሥራ የሚውል ማለትም "Supply and Construct Stone Masonry Works" ስራዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
- የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላችሁ፤
- VAT የተመዘገባችሁበትን ሰርተፊኬት ማቅረብ የምትችሉ፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin No.) ማቅረብ የምትችሉ፤
- ከመንግስት የግብር ዕዳ ነፃ መሆናቸው (Tax Clearance) ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ መስራቱን የሚያረጋግጥ የስራ ልምድ የማቅረብ ግዴታ ይኖርባቸዋል።
- ድርጅቱ ፋይናንሻል ፕሮፖዛል ማቅረብ የሚችልና አንዋል ተርን ኦቨር /Annual turnover/ 2,000,000 /ሁለት ሚሊዮን/ እና ከዚያ በላይ የሚያቀርብ ተጫራች መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከፕሮጀክቱ ፋይናንስ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በድርጅታችን የግዢ መመሪያ መሰረት በፕሮጀክታችን ትክክለኛ ስም MEKEL CON ENT YEGOFA YEM BET APP በባንክ በተረጋገጠ C.P.O ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ ብቻ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ሚያዝያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፕሮጀክቱ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ጎፋ አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት (17-05B) (ጎፋ ካምፕ ግቢ ውስጥ)
+251 118 886649/ +251 118 88 66 31
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ዋጋ ሞልታችሁ ከማቅረባችሁ በፊት ሳይቱን በአካል ተገኝታችሁ ማየት ይኖርባችኋል፡፡
በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የጎፋ 2 አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት (17-05B)
