Tender Detail

Tender Details

  • Company AA Kaliti Customs Office (አ.አ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት)
  • Address ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ ያለበት አዲሱ ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 4403766
  • Website
  • Deadline07 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-07 00:00:00
  • Categories Electrical And Electromechanical , Office And Home Furniture , Materials , Cloth And Shoes

በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶችን (የተሸከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። 

AA Kaliti Customs Office (አ.አ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት)


 

በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተያዙና የተወረሱ ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 40/2017

 

በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶችን (የተሸከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።  ከዚህ በታች በቅጹ በተጠቀሰው ቀንና ስዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃ ተዘጋጅቶ ከአርብ ሚያዝያ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ የሚታወቅ ሲሆን በተጨማሪም በግልጽ ዕቃ ጨረታ ላይ የሚሣተፉ ተጫራቾች ሰነዱን ኦክሸን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር ባመቻቸው የበየነ መረብ (Online) የመጫረቻ ሲስተም መተግበሪያ auction.et ላይ ከላይ በተጠቀሰው ቀን ጀምሮ የሚያገኙ መሆኑን እንገልጻለን።

በመሆኑም፡-

  1. በግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር ማንኛውም ተጫራቾች በዘርፉ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (CPO) መጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም በኦከሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር ባመቻቸው የመጫረቻ ሲስተም መተግበሪያ auction.et ላይ የሚወዳደሩ ተጫረቾች ሰነዶቹን በማያያዝ በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ።
  2. በጨረታው ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም።
  3. ተጫራቾች የዕቃዎችን የግልፅ ጨረታውን ሠነድ ከአርብ ሚያዝያ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመከፈል በቅ/ጽ/ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፣ በተጨማሪም የግልፅ ጨረታውን ሰነድ በኦክሽን ኢትዮጵያ አከሲዮን ማህበር ድረ-ገፅ auction.et ላይ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ያገኙታል።
  4. በዕቃ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) በቅ/ፅ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ።

 

ተ.ቁ

 

የቅ/ጽ/ቤቱ ስም

 

የጨረታው አይነት

 

የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ

የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

 

አ.አ ቃሊቲ ጉምሩከ ቅ/ፅ/ቤት

 

የእቃ ግልፅ

 

እስከ 28/08/2017 ዓ.ም

 

29/08/2017 ዓ.ም 3፡45 ሰዓት ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 4፡00 ሠዓት ይከፊል

 

  1. የጨረታው መከፈቻ ቦታ አአ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል። እንዲሁም በበይነ መረብ (Online) የሚጫረቱ ተጫራቾች በድረ-ገፁ መከታተል ይችላሉ።
  2. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል ወይም በኦከሽን ኢትዮጵያ አከሲዮን ማህበር ድረ-ገፅ auction.et ላይ ከተጫረቱ ደግሞ ከጨረታው በኃላ ይመለስላቸዋል።
  3. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል።
  4. ከላይ በተ/ቁ 8 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት CPO እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
  5. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩከ ፡ 011 - 470 - 85 03 እንዲሁም የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በአጭር የስልከ መስመር 9164 ወይም 09-05-11-55-11/ 0111-666 88 28 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

ማሳሰቢያ፡- በዕቃ ግልጽ ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች ከቀረቡት ሁለት የመጫረቻ አማራጮች መካከል በተመቻቸው በአንዱ ብቻ መጫረት የሚችሉ ሲሆን በአንድ ተጫራች ስም በሁለቱም አማራጮች መጫረት ከጨረታው የሚያስረዝ ይሆናል። በኦንላይን መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች በኦክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር ድረ-ገፅ መተግበሪያ auction.et መሰረት መሆኑን እየገለጽን ተጫራቾች የኦክሸን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ።

ስለሆነም በኦንላይን የተወዳደሩ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች የጨረታውን ሂደት በአካል መምጣት ሳያስፈልግ በቀጥታ (online) መከታተል ይችላሉ።

አድራሻ፡- ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው መንገድ ኖክ

ማደያ ያለበት አዲሱ ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቦሌ አትላስ ከለላ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢ.ቁ. 301

 

በአዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender