Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power)
  • Address ኮተቤ ብረታ ብረት መሣሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካ አካባቢ አቢሲንያ ባንክ ኪዳነምህረት ቅርንጫፍ ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-5-57-42-95
  • Websitehttps://www.eep.com.et/?lang=am
  • Deadline12 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-12 00:00:00
  • Categories Vehicles Rent

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለቆቃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ለሰርቪስ አገልግሎት የሚውል መኪና ኪራይ አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡-EEP/GOP/NCB/17/2017

 

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለቆቃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ለሰርቪስ አገልግሎት የሚውል መኪና ኪራይ አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በግዥ ኤጀንሲው ድረ-ገጽ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
  2. ተጫራቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታ ብረት አጠገብ ካለው አቢሲኒያ ባንክ ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ሰው ኃይል እና ፋይናንስ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ካሼር ቢሮ የማይመለስ ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በግዥ ክፍል ህንጻ ምድር ቤት ጀነሬሽን ኦፕሬሽን ግዥ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጸውን የአቅርቦት እና አገልግሎት ግዥ በሚመለከት የቴክኒካል እና የፋይናንሻል የመወዳደሪያ ሠነዳቸውን ዝርዝር በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/GOP/ NCB/17/2017 የሚል ምልክት በማድረግ 1 (አንድ) ኦሪጂናል እና 1 (አንድ) ኮፒ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) ከዚህ በታች በተገለጸው ሠንጠረዥ መሰረት የባንከ ክፍያ ትእዛዝ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power) ስም የተዘጋጀ ማቅረብ አለባቸው።

 

ተ.ቁ

 

የግዥው ዓይነት

 

የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን በብር

 

የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት

 

የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት

 

1

 

ለሰርቪስ አገልግሎት የሚውል መኪና ኪራይ አገልግሎት

ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር)

ግንቦት 04 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡00

ግንቦት 04 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡30

 

  1. ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-5-57-42-95 መደወል ይችላሉ ።
  2. ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

 

Save Tender