Tender Detail

Tender Details

  • Deadline12 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-12 00:00:00
  • Categories Construction Works

የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት በዋና መ/ቤት ግቢ ውስጥ አንድ የጥበቃ ማማ በግልፅ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 010/17

 

የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት በዋና መ/ቤት ግቢ ውስጥ አንድ የጥበቃ ማማ በግልፅ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

1ኛ. ማንኛውም በዘርፉ የታደሰ ደረጃ 7 (BC/GC) እና ከዚያ በላይ የአገልግሎት ፍቃድ ያለው፣ በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር / ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ተፈላጊ ሰነዶችን ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

2ኛ. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀን ሲሆን ሰነድ የሚሸጠው በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡30 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ አዲስ አባባ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 ሽያጭ ክፍል በመክፈል ደረሰኝ ይዘው ቢሮ ቁጥር 208 አቅርቦትና ኮንትራት አስተዳደር ቡድን ቢሮ በመምጣት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡

3ኛ የጨረታ ፖስታውን ፋይናንሻል እና ቅድመ መገምገሚያዎችን /ቴክኒካል ሰነድ/ በተለያየ ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት አሽጎ ማቅረብ አለባቸው፡፡

4ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በጨረታ ሰነድ ላይ የተገለፀውን ብር በሲፒኦ ወይም በባንክ ዋስትና ከቴክኒካል /ህጋዊ ሰነዶች/ ኦርጅናል ሰነድ ጋር ወይም ለብቻው በፖስታ አሽጎ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

5ኛ. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ይውልና በ15ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከ4፡30 ጀምሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡

6ኛ. የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።

7ኛ. ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ

አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ስልክ ቁጥር 0116-454147/0116-453598/0118 694931 ከሰዓሊተ ምህረት ማርያም ቤ/ክርስትያን ፊት ለፊት የሚገኘው ህንፃ

 

የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት

 

Save Tender