በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ባ/ዳር ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሰራተኞች አገልግሎት የሚውል ለአንድ አመት የሚቆይ የሰራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ፣ ፈርኒቸር ኮምፒውተር ቋሚ/እቃዎች ለአንድ አመት የሚቆይ የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 05/2017 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ባ/ዳር ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሰራተኞች አገልግሎት የሚውል ለአንድ አመት የሚቆይ የሰራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ፣ ፈርኒቸር ኮምፒውተር ቋሚ/እቃዎች ለአንድ አመት የሚቆይ የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች /አቅራቢዎች/ ከዚህ በታች የተጠየቁትን መስፈርቶችና ግዴታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ከጨረታው መልስ የሚከተሉትን ተጨማሪ ሰነዶች ያቀርባሉ።
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ የቲን ሰርተፍኬት ያላቸውና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል የታክስ ክሊራንስ የሚያገለግል ማቅረብ የሚችሉ ለሎት1 የባለቤትነት ማስረጃ፣ ወይም ሊብሬ፣ የአፕሬተርነት ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣ ለሎት 1 በዘርፉ ከተሰማሩ አካላት ማለትም የንግድ ስራ ፈቃዳቸው የየብስና ተዛማጅ አገልግሎት ሆኖ ሊብሬው ለንግድ የሚል ወይም የንግድ ስራ ፈቃዳቸው አገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሊብሬው የመኪና ማከራየት የሚል፤ አመታዊ የምርመራ ተለጣፊ ምልክት /ቦሎ/ ያደረገ፤
- ለሎት 2 እና ሎት 3 የሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ከ200.000 (ሁለት መቶ ሺ) ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ለአንድ ዓመት የሚቆይ የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት በዘርፉ ከተሰማሩ አካላት ማለትም ደረጃ ሶስት እና ከዚያ በላይ የንግድ ስራ ፈቃድ እና የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው
- የጨረታ ማስከበሪያ ከሎት 2 ሎት 3 የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% /ሁለት በመቶ እና ለሎት 1፡- ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ መስመር 10,000 /አስር ሺ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ለቋሚ እቃዎች ተጫራቾች በአገር ውስጥ የማምረቻ ወይም የመገጣጠሚያ ፋብሪካ ያላቸው ሲሆን ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሆኖ በቂ የመገጣጠሚያ ግብአት በመጋዘን ያላቸውና በአካል ማሳየት የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ለቋሚ እቃ ተጫራቾች የመገጣጠሚያ ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶችን በተመለከተ ዕቃዎችንና የአገልግሎት ዋጋን ጨምሮ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን አሸናፊ የሆነው ድርጅት የዕቃዎች ብዛት ወይም የአገልግሎቶችን አይነት ጠቅላላ ዋጋ ለማውጣት በአካል ጎንደር ጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያ በመገኘት ማወቅ ይጠበቅበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 100 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር በአፄ ቴዎድሮስ ክ/ከተማ ወደ ዲያስፖራ በሚወስደው አስፓልት መንገድ ዘመን ኮንስትራክሽን ድርጅት ጎን በሚገኘው የጉምሩክ ኮሚሽን ባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 304 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በጥንቃቄ በመሙላት በሚገባ በኢንቨሎፕ /ፖስታ/ በማሸግ እና ተቋሙ ያዘጋጀው ሰነድ ዋጋ መሙያው ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በግልጽ በማስቀመጥ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው እየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ 3ኛ ፎቅ የግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 306 ፎቅ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 16ኛው ቀን የህዝብ በዓል /እሁድ/ ከሆነ በ17ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን የንግድ ማስረጃዎች ኦርጅናል ለብቻው አቅርበው ማሳየት ይኖርባቸዋል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0583207051/0583206641/
0582263346/
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ባ/ዳር ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
