በደ/ኢ/ክ/መንግስት በኮንሶ ዞን የካ/መ/ደ/ሆስፒታል በ2017 በጀት ዓመት የተኝቶ ታካሚ ህክምና /IPD/ የጨቅላ ህፃናት ማገገምያ ክፍል / SC / የላቦራቶሪ /LABORATORY / እና የዋና ግንብ አጥር / FENCE / እድሳት ግንባታ በመንግሥት የግዥ መመሪያ መሠረት በግንባታ ዘርፍ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በደ/ኢ/ክ/መንግስት በኮንሶ ዞን የካራት መ/ደ/ሆስፒታል
የጨረታ ማስታወቂያ
መወዳደርያ መስፈርት ለካ/መ/ደሆስፒታል
በደ/ኢ/ክ/መንግስት በኮንሶ ዞን የካ/መ/ደ/ሆስፒታል በ2017 በጀት ዓመት የተኝቶ ታካሚ ህክምና /IPD/ የጨቅላ ህፃናት ማገገምያ ክፍል / SC / የላቦራቶሪ /LABORATORY / እና የዋና ግንብ አጥር / FENCE / እድሳት ግንባታ በመንግሥት የግዥ መመሪያ መሠረት በግንባታ ዘርፍ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በዘርፉ ለ2017 ዓ/ም የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፤
- የአቅራቢነት ንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤
- ህጋዊ የሰውነት ማረጋገጫ ያላቸው፤
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin No) ያለው ፤
- የ(Vat) ተመዝጋቢ የሆነና የምስክር ወረቀት ያለው፣
- የብቃት ማረጋገጫ GC እና BC-7 እና ከዚያ በላይ የሆነ፤
- የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሰነድ 50,000 /ሃምሳ ሺህ/ ብር ብቻ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ CPO በቴክኒካል ኦርጂናል ፖስታ ውስጥ በማድረግ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 /ሃያ አንድ/ ቀናት ቅዳሜ፤ እሁድ እና የበአላት ቀናትን ጨምሮ /ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 400 /አራት መቶ ብር/ ብቻ ክፍያና ሂሳብ ክፍል በመክፈል የከፈሉበትን ደረሰኝ በመያዝ ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጂናልና ሁለት ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ ተሞልቶ አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ በተለያየ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች በሁሉም ፖስታዎች ላይ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ስም ፊርማና አድራሻ በማሳረፍ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በማድረግና በትክክል በማሸግ በ22ኛው የሥራ ቀን 4፡00-4፡30 ሰዓት ላይ ሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ በአካል በመገኘት ለጨረታ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሳጥን የሚከፈተው በዚሁ ዕለት በ4፡31 ሰዓት ላይ ታሽጎ ከረፋዱ 4፡40 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ-
- ጨረታው የሚከፈትበት 22ኛው ቀን የመንግስት መደበኛ የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- በጨረታው መክፈቻ ዕለት ተጫራቾች በራሳቸው ፈቃድ አለመሟላት የጨረታ አከፋፈትን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሚሆን ድርጅት አሸናፊነቱ ተገልጾ በሚሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ተገቢውን መፈጸም አለበት፡፡
- አሸናፊው ከተለየ በኋላ ራሱን ከጨረታ የሚያገል ከሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመ/ቤቱ ውርስ ሆኖ አግባብ ባለው ህግ ይጠየቃል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 09-02-92-81-00 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል /ኢ/ክ/ መንግሥት በኮንሶ ዞን ካራት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል፡፡
በደ/ኢ/ክ/መንግስት በኮንሶ ዞን የካራት መ/ደ/ሆስፒታል
