Tender Detail

Tender Details

  • Company በደቡብ ኢት/ክልል መንግሥት ጎፋ ዞን ዑባ ደብረ ፀሐይ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ጎፋ ዞን ዑባ ደብረ ፀሐይ ወረዳ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline10 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-10 00:00:00
  • Categories Agriculture And Farming , Water Construction

በደቡብ ኢት/ክልል መንግሥት ጎፋ ዞን ዑባ ደብረ ፀሐይ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በወረዳው ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ካፒታል በጀት በውሃ ማዕድን ኢነ/ጽ/ቤት በኩል የመስኖ ግንባታ ሥራ እና የንጹህ መጠጥ ዉሃ ግንባታ ሥራ የሚውል የፋብሪካ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በደቡብ ኢት/ክልል መንግሥት ጎፋ ዞን ዑባ ደብረ ፀሐይ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በደቡብ ኢት/ክልል መንግሥት ጎፋ ዞን ዑባ ደብረ ፀሐይ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በወረዳው ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ካፒታል በጀት በውሃ ማዕድን ኢነ/ጽ/ቤት በኩል የመስኖ ግንባታ ሥራ እና የንጹህ መጠጥ ዉሃ ግንባታ ሥራ የሚውል የፋብሪካ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው።

  • በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው፤
  • የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፤
  • የግብር ከፋይነት ምዝገባ ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፤
  • የዘመኑ ግብር የከፈሉበት መረጃ ማቅረብ አለባቸው፣
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤
  • ቲን ነምበር ማቅረብ አለባቸው፤
  • ለጨረታው ሠነዱን የማይመለስ 200 ብር /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከዑባ ደብረ ፀሐይ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት መግዛት አለባቸው፤
  • የጨረታ ማስከበሪያ 2% /40,000/ ብር (አርባ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፤
  • ጨረታው የሚከፈትበት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሣጥኑ በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዕለቱ በ4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፤ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ ሥራ ቀን ይከፈታል፤
  • ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባይገኙም ጨረታውን ለመክፈት አያስተጓጉልም፤
  • ዋጋውን ዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ ሞልታችሁ ማኅተም ተደርጐ ተፈርሞበት በፖስታ ታሽጐ ኦሪጅናልና ኮፒ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ጨረታ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በ15 የመንግስት የሥራ ቀናት ማቅረብ አለባቸው፤
  • አሸናፊ ድርጅት ካሸነፈበት ቫትን ጨምሮ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ማስያዣ የጨረታ ማስከበሪያው ተመላሽ ይደረጋል፤
  • አሸናፊ ድርጅት /ግለሰብ/ ያሸነፈውን ዕቃ እስከ ጽ/ቤቱ ማድረስ ግዴታ አለበት፤

ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

በደቡብ ኢት/ክልል መንግሥት ጎፋ ዞን ዑባ

ደብረ ፀሐይ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender