ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃ/አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
SPA SERVICE ENTERPRISE (የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት)
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃ/አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት፡-
ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረታ የሚወጡ የዕቃ/የአገልገሎት ግዥ
ሎት 1 የመታሻ ዘይት /ፖራፊን ኦይል/ አቅርቦት ግዥ
ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች ማሟላት ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው
- ተጫራቾች በዘርፋ የተሰማሩበት ሕጋዊና የታደሰ የ2017 ዓ.ም ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ TIN እና VAT ሰርተፍኬት ያላቸው ፣ የገቢዎች ክሊራንስና ጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ የተሰጣቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር የምዝገባ ፈቃድ የተመዘገቡና የቅርብ ጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ማንኛውም ተጫራች የግዥ የጨረታ ማስከበሪያ 20,000.00 /ሃያ ሺ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ለጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በድርጅታችን አዲሱ ፍልውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመክፈል ከድርጅቱ ግዥ አቅርቦት ቡድን መሪ ቢሮ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊትና ከነቫቱ ተብሎ በኢትዮጵያ ብር መገለጽና መሆን አለበት፡፡ ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውንና ማህተም አሟልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሠነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም፤ ዕቃው የሚቀርብበት ጊዜ፣ ቦታና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መገለጽ አለበት፡፡ ስለ ዕቃው ዋስትናና የዋስትና ጊዜ በግልጽ መግለጽ አለበት፡፡
- ጨረታውን በሚመለከት ለማሸነፍ እንዲረዳዎት ለማንኛውም ኃላፊና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከጨረታ የሚሰረዝ ሲሆን አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ ይሰረዛል።
- ድርጅታችን የዋጋ ለውጥ ሳይኖር በመጠን ወይም በዋጋ እስከ 25% በመጨመር መግዛት እንደሚችል በቅድሚያ መታወቅ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 06 ቀን 2017 ዓም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው ጠዋት በዕለቱ 4:30 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሚጫረቱበትን የግዥ አይነት መሠረት የተሟላ የቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናሽያል በተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ - Bid document /መሰረት ጨረታ ሰነዳችሁ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ የጨረታው ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ ለብቻው እና ፋይናሽያል ሰነድ ለብቻው በጨረታ ሣጥኑ ማስገባ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሂደቱ የቴክኒክ ሰነድ ግምገማ እና ናሙና ጥራት ግምገማ ውጤት (40%) እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት (60%) ሲሆን ድምር ውጤት አሸናፊ የሚለይ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ፤ ነገር ግን ቴክኒካል፣ ናሙና ጥራትና ብቃት ግምገማ ያላለፈ ፋይናንሽያል እንደማይከፈት እንዲታወቅ፣ የመገምገሚያ መስፈርቶቹ በሚሰጠው የጨረታ ሰነድ ማየት ይቻላል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 0115 53 07 67/011 5 15 73 37
ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት
