በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ለ2017 ለሥራ የሚገለገልበትን Lot1. Uniform (የደንብ ልብስ እና ሸሚዝ) በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ለ2017 ለሥራ የሚገለገልበትን Lot1. Uniform (የደንብ ልብስ እና ሸሚዝ) በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
- ህጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፍዳቸውን ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (VAT) ያላቸው
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በሌላም በሚመለከታቸው ፍቃድ ሰጪ አካላት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቶች ብቻ መካፈል ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ የስራ ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በመ/ቤቱ ቀርቦ መግዛት ይችላል።
- ለጨረታው ማስከበሪያ ጠቅላላ ካቀረቡት የዕቃ ዋጋ ብር 1% በተረጋገጠ ባንክ (CPO) በድርጅቱ ስም አሰርቶ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የእቃውን ስፔስፊኬሽን ከድርጅቱ በቀረበው መሠረት በግልፅ በመጻፍና ዕቃው ላይም በግልጽ መታየት ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፁትን ማንኛውም ሁኔታዎች መለውጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫት ያጠቃለለና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎችን አሟልተው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የቢሾፍቱ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ቀርቦ ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚኖሩት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ተከታታይ ቀናት ጠብቆ በ15ኛ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ጨረታው ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው::
- ድርጅቱ ከሰጠው ስፔስፊኬሽን ውጪ ማስተካከያ ማድረግ እና መሰረዝ (Material Devation) አይቻልም::
- ከሎት ውስጥ ከተሰጡት ዕቃዎች ዝርዝር በከፊል መወዳደር (Partial Offer) አይቻልም::
- ተጫራቾች ከድርጅቱ በዋጋ ማቅረቢያ የድርጅቱ ኦርጅናል ማህተም የቢሾፍቱ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት የሚል ማህተም ባረፈበት ላይ ብቻ የዕቃ ዋጋዎችን ሞልቶ ማቅረብ አለበት፡፡ ከድርጅቱ ዋጋ ማቅረቢያ ውጪ የሚመጡ ሰነዶች ዋጋ የላቸውም፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ድርጅታችን ግዥ እና ፋይናንስ አስ/ስራ ሂደት በመቅረብ ወይም በስልከ ቁጥር 011-430-05-17 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ።
የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት
