በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ከሰም የገበሬዎች ሁለገብ ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒዬን ኃ.የተ ኬሚካል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ከሰም ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒዬን ኃ/የተ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ከሰም የገበሬዎች ሁለገብ ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒዬን ኃ.የተ ኬሚካል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ዩኒዬኑ ይገልፃል።
- የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /Tin number/ ማቅረብ የሚችል
- የጨረታ ማስከበሪያ ያቀረበውን ዋጋ 2% ሲፒኦ (cpo) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በተቋሙ አካውንት ገቢ በማድረግ ደረሰኙን ማያያዝ ሚችል
- የሚሞላው ዋጋ ማንኛውንም ወጭ ግብር /ዊዝሆልድ/ የሸፈነ መሆን አለበት
- ተጫራቾች ከአሁን በፊት በጨረታ አሸንፈው ውል ገብተው ስራው ለመስራት ፍቃደኛ ባለመሆን ያልተከሰሱ ወይም እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ኬሚካል ህጋዊ የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን እና ደጋፊ ሰነዶቻቸውን በአማርኛ ቋንቋ ማዘጋጀት አለባቸው፡፡
- ማስታወቂያው ጋዜጣ ላይ ከዋለበት ከቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ የጨረታ ሰነዱን 500 ብር ከፍለው ሰነዱን በመውሰድ በተቀመጠው ዝርዝር ሞልተው ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በጋዜጣ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
- የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋው በመጨረሻው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ሆኖ ጨረታው የሚከፈተው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 8፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
- ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ከሰም ዩኒዬን ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 022 223 01 27/ 04 88 / 0910367684 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ከሰም ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒዬን ኃ/የተ
