የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በሀዋሳ ከተማ አስ/ከተማ ልማትና ኮን/ መምሪያ በሮድ-ፈንድ በጀት ሊተገበር ካቀዳቸው ሥራዎች መካከል ለጠጠር መንገድ /ግራዊል ሮድ/ ግንባታ ጠጠር የማልበስ ሥራ ለማሰራት ለአምስቱ (5) ሎት ሥራ የሚሆን ሴሌክቲንግ ማቴሪያል ግዥ ለመፈጸም ያስፈለገ በመሆኑ በተዘጋጀው ዲዛይን ተጠቅሞ በዘርፉ ፈቃድ ካለው ድርጅት/ማህበራት መካከል በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
ጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በሀዋሳ ከተማ አስ/ከተማ ልማትና ኮን/ መምሪያ በሮድ-ፈንድ በጀት ሊተገበር ካቀዳቸው ሥራዎች መካከል ለጠጠር መንገድ /ግራዊል ሮድ/ ግንባታ ጠጠር የማልበስ ሥራ ለማሰራት ለአምስቱ (5) ሎት ሥራ የሚሆን ሴሌክቲንግ ማቴሪያል ግዥ ለመፈጸም ያስፈለገ በመሆኑ በተዘጋጀው ዲዛይን ተጠቅሞ በዘርፉ ፈቃድ ካለው ድርጅት/ማህበራት መካከል በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት -
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅት/ማህበር መወዳደር ይችላሉ፡-
- በኮንስትራክሽን ዘርፍ ደረጃ GC-9 ፍቃድ ያላቸው፤
- በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣
- ከክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን 2017 በጀት አመት የተመዘገበ የብቃት ማረጋገጫ ያሳደሱ መሆን አለባቸው።
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
- የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ) አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /በአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ወስዶ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት ፡፡
- ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ እና ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 (አሥራ አምስት) ተከታታይ ቀናት በፋይ/ኢኮ/ልማ/ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከቀኑ 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት፣ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል ፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 046-220-99-63/046-212-13-34
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና/ኢኮ/ልማት መምሪያ
ሀዋሳ
